Ethiopia - Collective Agreements Database



ኖቫስታር ጋርመንት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል/ማህበር

እና


በመሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር መካከል 

ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ የህብረት ስምምነት



የካቲት 2008ዓ.ም 

ማውጫ

ተ.ቁ

ርዕስ

አንቀጽ

ገጽ


የስምምነቱ ዓላማ 

1

1


ትርጉም 

2



መብት ግዴታ 

  1. የድርጅቱ መብት 
  2. የድርጅቱ ግዴታ 

3

3

3

2

2

3


የማህበሩ መብትና ግዴታ 

  1. የማህበሩ መብት 
  2. የማህበሩ ግዴታ 

4

4

4

4

4

5-6 


የሠራተኛው ለማህበሩ አባልነት የሚያደርገው መዋጮ 

6


ስለሠራተኛ ቅነሳ 

7

7


የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች 

  1. ያለ ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብቱ ከባድ ጥፋቶች
  2. ደረጃ በደረጃ የሚያስቀምጡ ጥፋቶች  

8

9

9-10 

7-8

9-11

9-11


የቅጣት የጊዜ ገደብ 

12 


የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ 

10 

12 


ቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት 

11

12 


የደረጃ እድገት 

12

13


የደረጃ ዕድገት 

12

13


ዝውውር 

13

14


ሥልጠና 

14

15


የሠራተኞች ጤንነትና ደህንነት ጥበቃ 

15

15


ውጤታማነት 

16

15


የምስክር ወረቀት 

17

16


የሙከራ ጊዜ 

18

16


ስለ ሥራ ስንብትና ካሳ ክፍያ 

19

17


የሥራ ሰዓት 

20

18


ስለ ትርፍ ሰዓት ሥራና ክፍያ 

21

18


የሳምንት የእረፍት ጊዜ 

22

18


ህዝብ በዓላት 

23

18


ስለ ፈቃድ 

24

18-19


የህመም ፈቃድ 

25

20


የወሊድ ፈቃድ 

26

20-21 


የሃዘን ፈቃድ 

27

22


በስራ ላይ ስለሚመጡ ገዳቶች 

28

22


የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ 

29

23-24 


የአደጋ መከላከያና የደንብ ልብስ 

30

25


የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም 

31

26


የደመወዝ ጭማሪ 

32

27 


በቦነስ /ጉርሻ/

33

27


የሻይ ቤትና የስፖርት ክለብ 

34

28 


በፍርድ ስለሚታሰሩ ሠራተኞች 

35

28 


ስለ መልዕክት 

36

28 


ልዩ ልዩ ጥቅሞች 

37

28 


ውሎ አበል 

38

29


ዓመታዊ ብድር 

39

30 


ለጊዜው ስለሚደረግ እገዳ 

40

30


የሥራ ውል መቋረጥ ስለሚደረግ ክፍያ 

41

30


ደመወዝ ቅነሳ 

42

30


የይርጋ ጊዜ 

43

31


ሥራ ማቆምና መዝጋት 

44

31


የህጎች ውጤት/የህግ አፈጻጸም 

45

31


ስምምነቱን ሥራ ላይ ስለማዋልና የሚጸናበት ጊዜ 

46

31

ይህ የህብረት ስምምነት ስለ ሠራተኛ ጉዳይ በወጣው ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት “አሰሪ” እየተባለ በሚጠራው በኖቫስታር ጋርመንት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሠራተኞች ማህበር መካከል ዛሬ 14/03/2009 (እ/ኤ/አ) ተፈርሟል፡፡ 

አንቀጽ አንድ

የስምምነቱ ዓላማ

ይህ የህብረት ስምምነት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ያካትታል፡፡

  1. የድርጅቱን ህልውና እና አቋም እንዲሁም የሠራተኛውን መብት መጠበቅ ማጠናከርና ማሳደግ፣ 
  2. የድርጅቱን ዓላማ ግብ እንዲመታ ማድረግ፣
  3. የድርጅቱን የሥራ ዘዴዎች እየተሻሻሉ ዘመናዊ አቋም እንዲኖረው ማድረግ፣ 
  4. የዲሲፒሊንና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓትን በግልት ለማሽቀመፅ፣ 
  5. በድርጅቱ ውስጥ የሰው ጉልበት፣ ጥሬ እቃ፣ መሣሪያዎችና ገንዘብ በሚገባ በሥራ ላይ የሚውልበትን መንገድ መሻት፣
  6. የሠራተኞች ጤንነት ደህንነት መጠቢያ ዘዴዎን መሠሪያዎችን የሚሻሻሉበትን መንገድ መፈለግ፣ 
  7. ለሠራተኞች የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ስለሚደራጁት ሁኔታ መወሰን፣ 
  8. በሠራተኛው መካከል የውድድርና የሥራ ፍላጎት መንፈስ እንዲያድግ በሥራ ብልጫ ለሚያሳዩ ሠራተኞች የማበረታቻ ዘዴ እንዲፈጠር ለማድረግ፣ 
  9. ሠራተኛው የድርጅቱን እቅድና ክንውን ለመገምገም የመብትም የግዴታም ጉዳይ መሆኑን ለመጠቆም፣ 
  10. የኢንድስትሪ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ፣ 

አንቀጽ ሁለት

ትርጉም /ትርጓሜ/

  1. ድርጅት ወይም አሰሪ ማለት ኖቫስታር ጋርመንት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሠራተኞች ማህበር ነው፡፡ 
  2. ሠራተኛ ማህበር ማለት ኖቫስታር ጋርመንት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር ነው፡፡ 
  3. ሠራተኛ ማለት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 2/3 የተሰጠው ትርጉም የሚኖረው ሲሆን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የአስተዳደር ሥራ አስኪያጅ፣ የንግድ ሥራ አስኪያጅ የፋይናንስ ሥራ አስኪያጅ የምርትና ቴክኒክ ሥራ አስኪያጅ፣ (የጥራት ቁጥጥር አገልግሎት ኃላፊ) የኦዲት አገልግሎት ኃላፊ እንዲሁም ለወደፊት የሚፈጠሩ ተመሳሳይ የሥራ ኃላፊዎችን አይጨምርም፡፡ 
  4. የተጣራ ትርፍ ማለት ታክስ ከተቀነሰ በኋላ ያለው ትርፍ ነው፡፡ 
  5. አዋጅ ማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ነው፡፡ 
  6. ሚኒስቴር ማለት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡ 
  7. ደመወዝ ማለት አንድ ሠራተኛ በሥራ ጊዜው በደንቡ መሠረት አስፈቅዶ ለመቅረት የሚያስችለው ሁኔታ ነው፡፡ 
  8. ፈቃድ ማለት በዚህ የህብረት ስምምነት በተደረገው መሰረት ሰራተኛው ደመወዝ እየተከፈለው ወይም ሳይከፈለው ከመደበኛ የስራ ጊዜው በደንቡ መሰረት አስፈቅዶ ለመቅረት የሚያስችለው ሁኔታ ነው፡፡ 
  9. የጉዳት ካሳ ማለት ከስራ ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ በሠራተኛው ላይ ለደረሰው አደጋ የሚከፈል ካሳ ማለት ነው፡፡ 
  10. ትርፍ የሥራ ሰዓት ማለት በዚህ የህብረት ስምምነት ከተወሰነው መደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ ሰራተኛው የሰራበት/ የሚሰራው ሰዓት ማለት ነው፡፡ 
  11. ከሥራ ጋር ግንኙነት ያለው አደጋ ማለት ሠራተኛው በምድብ ሥራው ላይ እያለ በስራው ላይ እያለ በሥራው ምክንያት የሚደርስ አደጋ ነው፡፡ 


አንቀጽ ሶስት

መብትና ግዴታ /መብትና የውዴታ ግዴታ/


የድርጅቱ /የአሰሪና የውዴታ ግዴታ መብት/

በዚህ ህብረት ስምምነትና በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 ድንጋጌዎች መንፈስ ድርጅቱ ከሥራ ውል በመነጨ የሰራተኛውን የሥራ እንቅስቃሴና ክንውን የመምራት የማስተዳደርና የመቆጣጠር ሥራውን ለማሰራት እቅድ ለማውጣትና ለመፈጸም እንዲሁም ሠራተኞችን ለመቅጠር ለማዘዋወርና ህጋዊ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ለመውሰድ ወዘተ ያለውን መብት ማህበሩ ያውቃል፡፡ 

እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 29 ተራ ቁጥር 3 መሠረት ሰራተኛ ለመቀነስ መብት አለው፡፡ 

  1. ድርጅቱ /የአሰሪ ግዴታዎች/

ድርጅቱ ሠራተኞችን በሚመለከቱ የመንግስት ህጎች፣ አዋጆች መመሪያዎች እንዲሁም በህብረት ስምምነቱ ውስጥ የተመለከቱትን ሁሉ በሚገባ ያከብራል፡፡ 

ከዚህ በላይ በተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን ድርጅቱ የሚከተሉትን ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡

  1. የሠራተኞች ጤንነትና ደህንነት እንዲሁም ሰብዓዊ ክብር ለመጠበቅ ተገቢ ጥንቃቄዎች ያደርጋል፡፡ 
  2. ሠራተኞች በሙያም ሆነ በእውቀት እንዲሻሻሉ ከሚደረግ መንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ጋር ይተባበራል፡፡ 
  3. ማንኛውም ሠራተኛ የማህበሩ አባል ወይም የሥራ አመራር ተካፋይ በመሆኑ ድርጅቱ /አሰሪው በመሆኑ ምክንያት /በማህበሩ/ሥራ ተጽዕኖ /አድእሎ/ አያደርግበትም፡፡ 
  4. ሊከፍል የተስማማበትን ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡ 
  5. በህግ ወይም በዚህ የህብረት ስምምነት ሠራተኛው ያገኘውን ህጋዊ መብት ሚጥስ ወይም ሊቀንስ የሚል ማንኛውንም ተግባር በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ መንገድ አይፈጽምም እንዲሁም በማህበሩ ላይ ህገ ወጥ ተግባር መፈጸም የለበትም፡፡  
  6. ሠራተኛው መብትና ተግባር ግዴታውን እንዲያውቅ ከማህበሩ ጋር በመመካከር አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ 
  7. ለድርጅቱ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን አሟልቶ ያቀርባል፡፡ 
  8. እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚሰራውን ሥራና የኃላፊነቱን ወሰን የሚያሳይ የሥራ መደብ ዝርዝር መግለጫ ያዘጋጃል፡፡ የሚያዘጋጀውም የስራ ዝርዝር በስራ መደቦች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ 
  9. ከሰራተኛው ቁጥጥር ውጭ በመሳሪያው አለመስተካከል ወይም አለመሟላት ወይም ብልሽት የሰራተኛው አለመሆኑ በባለሙያው ከተረጋገጠ ሠራተኛውንም አያስጠይቀውም /አያስቀጣውም/፡፡ 
  10. ሌሎች በሕግ የተደገፈ እርምጃዎች እንደ ሁኔታው የመውሰድ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ሠራተኛው ለመስራት ዝግጁ ሆኖ ነገር ግን ድርጅቱ ከአቅሙ በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሥራ ባይሰጠው ለሠራተኛው ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ 
  11. የሠራተኛ ቅነሳ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ መሠረት እንደገና ታይቶ እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡ 
  12. በሥራና በሰራተኛው ላይ ችግር ሲደርስ ወይም ያደርሳል ተብሎ ሲገመት ድርጅቱ ከማህበሩ ጋር አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ መፍትሔ እንዲገኝለት ያደርጋል፡፡ 
  13. በድርጅቱ ጥፋት ወይም ግዴለሽነት በሠራተኛው ላይ ለሚደርሰው አደጋ ወይም በሽታ ድርጅቱ ተጠያቂ ነው፡፡ 
  14. በድርጅቱ ማንኛውንም ሠራተኛ በሚመለከት በዚህ ህብረት ስምምነት የተጠቀሱትን ጉዳዮች ማህበሩ ሳያውቅ ለማሻሻል ለመሰረዝ ወይም ለመለወጥ አይችልም፡፡ 
  15. በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙትን ማንኛውም የውስጥ እድገት ከሰራተኛ ማህበሩ አመራር ጋር በጋራ በመወያየት እድገት የሚያገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ 
  16. ሠራተኛው በሥራ ላይ ከሥራ ወደ ቤት ወይም ከቤት ወደ ሥራ ሲመለስ በሥራ ምክንያት ለሚደርስበት አደጋ የሚባክነውን ሰዓት በተመለከተ አሠሪው ተገቢውን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ 

አንቀጽ 4

የማህበሩ መብትና ግዴታ

4.1. የማህበሩ መብት 

4.1.1. ማህበሩ ማንኛውንም ሠራተኛ በሚመለከት በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ከድርጅቱ ወይም ከአሰሪው ጋር በመነጋገር ለማሻሻል፣ ለመሰረዝ ወይም ለመለወጥ ይቻላል፡፡ 

4.1.2. በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ የተመለከቱትንም ሆነ ወይም ከስምንነቱ ውጪ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ማናቸውም የሥራ ሁኔታዎች ሠራተኛውን ወክሎ ከአሰሪው ጋር የሚነጋገር ሠራተኛ ማህበሩ መሆኑን ድርጅቱ ያውቃል፡፡ 

14.1.3. የማህበሩ የሥም አመራር አባል የሆነ ማንኛውም ሠራተኛ መደበኛ ሥራውን በማያውክ ሁኔታ በማህበሩ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለ ተጽዕኖ ተካፋይ መሆን ይችላል፡፡ 

4.1.4. ሠራተኛውን በሚመለከት መግለጫዎችን በቅድሚያ ድርጅቱ በቅድሚያ ድርጅቱንና ማህበሩ በመነጋገር ምርትን በማይጎዳ ሁኔታ ቀኑን ይወስናሉ፡፡ 

4.1.5. ለማህበሩ ተግባር አባሎችን ለመሰብሰብ ሲያስፈልግ በቅድሚያ ድርጅቱንና ማህበሩ በመነጋገር ምርትን በማይጎዳ ሁኔታ ቀኑን ይወስናሉ፡፡ 

4.2. የማህበሩ ግዴታ 

4.2.1. ሠራተኛው የህብረት ስምምነቱን አንቀጾች ትርጉም እንዲረዳ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ 

4.2.2. ይህን ህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም ስለአዳዲስ የሥራ ሁኔታ ለውይይት አሠሪው የሚያወጣቸውን አስፈላጊው የሆኑ መመሪያዎችንና እቅዶን ለማስፈጸም ለሚያደርገው ሁሉ ማህበሩ ድጋፍና ትብብር ያደርጋል፡፡ 

4.2.3. የህብረት ስምምነት ህጎችንና መንግስታዊ መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ አሰሪው የሚያወጣቸውን አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎን እቅዶን ለማስፈጸም ለሚያደርገው ሁሉ ማህበሩ ድጋፍና ትብብር ያደርጋል፡፡ 

4.2.4. በድርጅቱና በሠራተኛው መካከል ቅሬታ የሚፈጠር ውዝግብ አሉባልታ እንዳይነሳ ጥረት ያደርጋል፡፡ 

4.2.5. በመንግስት የሚወጡት ልዩ ልዩ መመሪያዎች ሠራተኛው በቀና መንፈስ እንዲቀበለው ያደርጋል፡፡ 

4.2.6. የፋብሪካው ምርት እንዲዳብር አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ 

አንቀጽ አምስት

የሠራተኛው ግዴታዎች

ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 13፣14/2፣98 እና 94 የተገለጹ ግዴታዎችን ማክበሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ግዴታዎች የማክበርና የመፈጸም ኃላፊነት አለበት፡፡ 

5.1. ስለ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣውን አዋጅ፣ ደንቦች ይህን የህብረት ስምምነት እንዲሁም በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ወደ ፊት የሚወጡትን ማሻሻያዎችንና የህብረት ስምምነቱን ሳይቃረን አሰሪው በየጊዜው የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ማክበርና ሥራ ላይ ማዋል አለበት፡፡ 

5.2. ሠራተኛው ለተቀጠረበት ሥራ መላ ጉልበቱንና ችሎታውን በመስጠት የድርጅቱ የሥራ ውጤት እንዲዳብር በትጋትና በጥንቃቄ መስራት አለበት፡፡ 

5.3. ሠራተኛው ችሎታው እስኪፈቀድለት ድረስ ከድርጅቱ የተሰጠውን የሥራ መመሪያ ወይም የተመደበበትን ሥራ በሚገባ መፈጸም አለበት፡፡ 

5.4. ሠራተኛው ሥራውን ለማከናወን የሚጎልባቸውን የደንብ ልብስ ወይም የሥ ልብስ ወይም ማንኛውንም መሳሪያ ወይም እቃ በጥሩ ሁኔታ መጠበቅና መያዝ አለበት፡፡ 

5.5. የድርጅቱን የሥነ ሥርዓተ ደንቦች ማክበር አለበት፡፡ 

5.6. የራሱን የሥራ ጓደኛውንና ማንኛውንም የአሰሪውን ንብረት ሊጎዳ የሚችል አደጋ ከመፈፀም እራሱን መግታት አለበት፡፡ 

5.7. የራሱን፣ የሥራ ጓደኛውንና በማንኛውም እንግዳ ሰው ላይ ጉዳት የሚያስከትል ድንገተኛ አደጋ የሥራ ክፍሉ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በማንኛውም ጊዜ እርዳታውን ማበርከት አለበት፡፡ 

5.8. በቅድሚያ ድርጅቱን ካላስፈቀደ በስተቀር የአሰሪው ንብረት የሆነውን ማንኛውንም የድርጅቱን መሳሪያ ወይንም ሀብት ለግል ጥቅሙ መገልገል የለበትም፡፡ 

5.9. በስካር መንፈስ ስራ ላይ መገኘት የለበትም፡፡ 

5.10. ሁልጊዜ የራሱንና የድርጅቱን ስም መጠበቅና መልካም ጠባይ ይዞ መገኘት አለበት፡፡ 

5.11. በአሰሪው ወይም በሰራተኛው ማህበር መካከል አለመግባባት የሚፈጥር ሀሰተኛ ወሬ እና ጠብ ለማንሳት ወይም ፀብ እንዲነሳ ከመሞከር መቆጠብ አለበት፡፡ 

5.12. ለድርጅቱ ሥራ ሲባል ደመወዝን፣ ጥቅምንና ደረጃውን የማይነካ ሆኖ ሲገኝ የሥራ ትዕዛዝ የመቀበልና የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ 

5.13. ፈቃድ ለመጠየቅ የሚያስችል ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመው በስተቀር ከክፍሉ ሳያስፈቅድ ከሥራ መቅረት የለበትም ችግር ገጥሞት ከቀረ የቀረበትን ምክንያት በቂ የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ 

5.14. ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ጊዜ የክፍል አለቃውን ሳያስፈቅድ ከስራ ቦታው ተነስቶ መዘዋወር የለበትም፡፡ 

5.15. ማንኛውም ሰራተኛ የተሰጠውን የሥራ ልብስ በስራው ላይ ለብሶ መገኘት አለበት፡፡ ከግቢ ውጪም ከሥራ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታው የስራ ልብሱን ለብሶ መገኘት የለበትም፡፡ 

5.16. በድርጅቱ ወይም በድርጅቱ መሳሪያዎች ላይ፣ በሰራተኛው ደህንነትና ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሁኔታ ሲያጋጥም ወዲያውኑ ለቅረብ አለቃው ማሳወቅ አለበት፡፡ 

5.17. በአጠቃላይ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/19996 

አንቀጽ 13 ተራ ቁጥር 1 – 7 

አንቀጽ 14 ተራ ቁጥር 2 

አንቀጽ 93፣ 94፣ 157 እና 158 መብትና ግዴታ አፈጻፀማቸውን እንዲያከብሩ ማድረግ አለበት፡፡     


አንቀጽ ስድስት

ሠራተኛ ለማህበር አባልነት የሚያደርገው መዋጮ 

ሠራተኛው ለማህበሩ ሊያደርግ የተስማማውን መዋጮ ከሠራተኛ ማህበሩ በደረሰው ስም ዝርዝር መሰረት ድርጅቱ ከእያንዳንዱ ሠራተኛ ደመወዝ በመቁረጥ ለማህበሩ የተሰበሰበውን ገንዘብ በቼም ያስረክባል፡፡ ማህበሩም ለድርጅቱ ህጋዊ ደረሰኝ ይሰጣል፡፡ 

አንቀጽ ሰባት

ስለ ሰራተኛ ቅነሳ

በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 28 የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ፋብሪካው የሠራተኛ ቅነሳ ማድረግ ይችላል፡፡ ቅነሳ የሚያደርገው በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት ነው፡፡ 


አንቀጽ ስምንት

የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች

8.1. ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብቱ ከባድ ጥፋቶች ከአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27 በተጨማሪ አንድ ሠራተኛ ቀጥሎ የተመለከቱትን ጥፋቶች ለመፈጸሙ በማስረጃ ከተረጋገጠ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ይሰናበታል፡፡ 

8.1.1. የድርጅቱን ንብረት ወይም ገንዘብ መስረቅ እምነት ማጎደል 

8.1.2. በድርጅቱ ውስጥ ተቀጥሮ በሚሰራበት ጊዜ የሃሰት ወረቀት ወይም የሃሰት የገንዘብ ማስረጃ ሰነዶች ማቅረብ 

8.1.3. በድርጅቱ መሳሪያና እቃ ላይ ሆን ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ/ ወይም ለማድረስ መሞከር/ 

8.1.4. በስራ ቦታ ሲጋራ ማጨስ 

8.1.5. የድርጅቱ ተሽከርካሪ ለግል ጥቅም የተገለገለ ወይም ሶስተኛ ወገን እንዲገለገልበት ማድረግ 

8.1.6. የመንጃ ፈቃድ ከሌለው ግለሰብ ሆነ መንጃ ፈቃድ ኖሮት ላልተፈቀደለት ሰው ተሸከርካሪ መስጠት 

8.1.7. የፋብሪካውም ምርት ገበያ እንዲቀጣ በግልፅ ማጥላላት 

8.1.8 ጉቦ መስጠት ወይም መቀበል 

8.1.9. የፋብሪካው ጥቅም የሚጎዳ ሚስጥር ማውጣትና መናገር ለማይገባው ሰው መንደር ወይም የፋብሪካውን ህልውና የሚነካ ሚስጥር ማባከን 

8.1.10. አጥር ሾልኮ ወይም ከመደበኛ መግቢያና መውጫ በር ውጪ ወደ ፋብሪካ መግባት ወይም መውጣት በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ዝሙት መፈጸም ወይም ለመፈጸም መሞከር 

8.1.11. ሠራተኛውን ለአድማ ማነሳሳትና ሁከት እንዲፈጠር ማድረግ፡፡


8.2. በሥነ ሥርዓት ጉድለት ላይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የወጣ መመሪያ 

ተራ 

ዝርዝር

የመጀመሪያ ደረጃ

ሁለተኛ ደረጃ

ሶስተኛ ደረጃ


የመሥራት ችሎታ እያለው ሆን ብሎ ሥራን የማዳከም ተግባር መፈጸምና በሥራ ላይ ቸልተኛ መሆን 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በቅርብ አለቃ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመመሪያ ኃላፊ 

ስንብትን በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኃላ 


በተደጋጋሚ አርፍዶ ሥራ መግባት ወይም ቀድሞ ከሥራ መውጣት 

ማስጠንቀቂያ በክፍል ኃላፊ ከቅርብ አለቃ/ ሱፐርቫይዘር/ በቀረበ 

ሁለተኛ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በክፍል ኃላፊ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመመሪያ ኃላፊ 


አለበቂ ምክንያት ከ1-2 ቀን ከሥራ የቀረ 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ያልሠሩበት ደመወዝ ቅጣት በክፍል ኃላፊ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና ያልሠሩበት ቀን ደመወዝ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመመሪያ ኃላፊ  

ስንብትን በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


ከ3-4 ቀን በተከታታይ 

የመጨረሻ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመምሪያ ኃላፊ 

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ በመምሪያ ኃላፊ 



ለአምስት የሥራ ቀናት በተከታታይ ወይም በአንድ ወር ውስጥ በጠቅላላው ለአስር የሥራ ቀናት ወይም በአንድ ዓመት ውስጥ በጠቅላላው ለ30 ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከሥራ መቅረት 

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ  




የቅርብ አለቃን ትዕዛዝ አለመቀበል፣ ተቀብሎ ተግባራዊ አለማድረግ 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በቅርብ አለቃ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመምሪያ ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋ/ሥራ/አስኪያጅ ከፀደቀ በኃላ 


በሠራተኛው መካከል አሉባልታ መንዛት በወሬ ማሸበር የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ሠራተኛ ማሳደም፣ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያ ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና/ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኃላ 



ለብድር ለውሎ አበል ወይም ለትራንስፖርት በቅድሚያ የጠወሰደውን ሂሳብ በወቅቱ አለማወራረድ  

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በክፍል ኃላፊ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመምሪያ ኃላፊ 

ስንበት በሰው ኃላፊ አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኃላ 


ድርጅጹ ሽለ ደህንነት ያወጣቸውን ደንቦችና የአሰራር መመሪያን አለማክበር 

የመጨረሻ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያው ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



ድርጅቱን የድርጅቱን ሠራተኞች ወይንም የድርጅቱን ደንቦች አጭበርብሮ መገኘት፣ ሰንድ መደለዝ ማታለል፣ ማጉላላት 

ስንብትን በሰው ሃይል አስተዳደር በዋና ስራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 




በስራ ሰዓት ተኘቶ መገኘት ወይም ማንቀላፋት 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በቅርብ አለቃ  

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያው ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ስራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


የቅርብ አለቃን አለማክበር እና ተገቢ ያልሆነ የድፍረትና የማንቋሸሽ ተግባር መፈጸም 

የቃል ማስጠንቀቂያ በክፍል ኃላፊ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያው ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


ተሰጠውን ሥራ በወቅቱና በጥራት ሠርቶ አለማስረከብ፣ ራስን ለማሻሻል ጥረት ለማድረግ ያልቻለ 

የቃል ማስጠንቀቂያ በክፍል ኃላፊ በስራ ግምገማ ላይ ተመስርቶ 

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያው ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


የስርቆት ተግባር መፈጸም 

ስንብት በሰው ሃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 




የድርጅቱን ተሸከርካሪ ያለፈቃድ መንዳት 

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ 

ስንብት በሰው ሃይል አስተዳደር በዋና ስራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



በማንኛውም የስራ ሰዓት መጠጥ ጠጥቶ መገኘትና አደንዛዥ እዕቀቃ መጠቀም 

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያ ኃላፊ 

ስንብት በሰው ሃይል አስተዳደር በዋና ስራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



በማንኛውም የሥራ ሰዓት ያለበቂ ምክንያት ከቢሮ ቢሮ፣ ከክፍል ክፍል፣ መዟዟር በሥራ ቦታ አለመገኘት ሌላውን ሠራተኛ እየዞሩ ማዋራት 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በቅረብ አለቃ 

የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያው ኃላፊ 

ስንብት በሰው ሃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


በድርጅቱ ተሸከርካሪ ግጭት ፈጥሮ ለሥራ ኃላፊ ለመንግስታዊ አካል ወይም ለትራፊክ ፖሊስ በወቅቱ ሳያሳውቅ መቅረት 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሃላፊ ሆኖም ጥፋቱ ከባድና የሚያስጠይቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ 

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



በድርጅቱ የሥራ ሰዓት የግል ሥራን ማከናወነን 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በክፍል ኃላፊ ከ1 ቀን እገዳ ጋር  

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ስራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



የሥራ ባልደረጋ፣ ደንበኝንና አለቃን መሳደብ 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በቅርብ አለቃ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያ ኃላፊ 

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 


በስም የተጻፈ ደብዳቤ ወይም ማስጠንቀቂያ አልቀበልም ወይም ለጥያቄ አልቀርብም ያለ 

ለአንድ ወር ከሥራና ከደመወዝ ማገድ በመምሪያ ኃላፊ 

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



በስራ ቦታ አምባጓሮ ማሳየት ለፀብ የሚዳርግ ሁኔታዎችን ማሳየት 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያ ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



በስራ ቦታ መደባደብ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 




ለፍተሻ ተባባሪ ያለመሆን 

ተገድዶ እንዲፈተሽ ተደርጎ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመምሪያ ኃላፊ 

ስንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 



ሆን ብሎ የሌላውን ሠራተኛ የቀሪ መቆጣጠሪያ ካርድ ያስመታ 

የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በክፍል ኃላፊ 

የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከ1 ቀን እገዳ ጋር በመምሪያ ኃላፊ  

ሥንብት በሰው ኃይል አስተዳደር በዋና ሥራ አስኪያጅ ከፀደቀ በኋላ 

 


 



አንቀጽ ዘጠኝ

የቅጣት የጊዜ ገደብ

9.1. በአንቀጽ 8 ተራ ቁጥር 2 ከተመለከቱት ቀላል ጥፋቶች አንዱን አጥፍቶ ከተቀጣ በኋላ እስከ 1 ዓመት ድረስ ሌላ ጥፋት ካላጠፋ ቅጣቱ ይሰረዝለታል፡፡ ሆኖም ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ የቅርብ አለቃው በጎ አስተያየት ስለሰራተኛው በጽሁፍ ካቀረበ ቅጣቱ ሊነሳለት ይችላል፡፡ መረጃው ግን ከማህደሩ አይወጣም፡፡ 

9.2. በአንቀጽ 8 ከተዘረዘሩት ውጭ ለሚፈፀሙ ጥፋቶች ከተዘረዘሩት ጥፋቶች ጋር በማመዛዘን ተመጣጣኝ ቅጣት ይወስዳል፡፡ 

9.3. አንድ ሠራተኛ በአንድ የጥፋት ዓይነት ቅጣት ከተቀጣ በኋላ በ1ዓመት ጊዜ ውስጥ በሌላ ጥፋት ላይ ቢገኝ የጥፋቱ ክብደት ታይቶ ሌሎች ተመሳሳይ እርምጃዎች ይወስድበታል፡፡ 

አንቀጽ አስር 

የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች 

አጥፊ ሠራተኛ የሚገኝበት ክፍል የሥራ ኃላፊ ለሚያቀርበው የሥነ ሥርዓት እርምጃ ጥፋቶች በመረጃ ተደግፈው ሲቀርቡ ቅጣቱ በአስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ የሚወሰን ሲሆን የሥራ ስንብቱ ግን በዋና ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡  

አንቀጽ አስራ አንድ 

የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት 

  • የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በሚከተለው ሁኔታ ይፈጸማል፡፡ 

ዓላማው በቅጣት ላይ ብቻ ያተኮረ እንዳልሆነና ሠራተኛውን የድርጅቱ ጎጂና ጠቃሚ አካሄድ በነጻነት ሀሳብን በማሸራሸር በመጠቀም ተሳታፊ አድርጎ የባለቤትነት ስሜት ለመፍጠር 

  1. አንድ ሠራተኛ በተወሰደበት እርምጃ ወይም በሌላ ሁኔታ ቅሬታ ከተሰማው ውሳኔው በደረሰው በሶስት ቀን ውስጥ ለማህበሩ በማሳወቅ እርምጃ ለወሰደበት ኃላፊ ቅሬታውን ያቀርባል፡፡ 
  2. ቅሬታው የቀረበለት ኃላፊ በሶስት ቀን ውስጥ የበኩሉን ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢ አሁንም ቅሬታው ካልተወገደለት በሶስት ቀን ውስጥ ለአስተዳደር መምሪያ ያቀርባል፡፡ ኃላፊውም በአምስት ቀን ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡  
  3. በመምሪያ ደረጃ የተወሰዱ እርምጃዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች በዋና ሥራ አስኪያጅ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 
  4. በንዑስ አንቀጽ 11.1 እና 11.2 የቅሬታ አቀራረብ ደንብ እንደገለጸው ቅሬታ አቅራቢ በጊዜ ገደብ ቅሬታውን ካላቀረበ ቅጣቱን እንደተገለፀው ቅሬታ አቅራቢ በጊዜው ገደብ ቅሬታውን ካላቀረበ ቅጣቱን እንደተቀበለ ውሳኔ ሰጪው በጊዜው ገደብ ካልሰጠ ቅጣቱ እንደተነሳ ይቆጠራል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ሁለት 

የደረጃ እድገት 

12.1. በድርጅቱ ውስጥ ክፍት የሥራ መደብ ሲኖር አሠሪው በውስጥ ማስታወቂያ ለሠራተኛው ማሳወቅ አለበት፡፡ ለሥራ መደቡ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሠራተኞችን መርጦ ያወዳድራል፡፡ 

12.2. የደረጃ እድገት ያገኘ ሠራተኛ ለቦታው መነሻ ተብሎ የተወሰነውን ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያገኛል፡፡ 

12.3. የሠራተኞች የደረጃ እድገት ውድድር ውጤት እኩል ከሆ በጽሁፍ ወይም በተግባር ፈተና ተወዳድሮ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 

12.4. በደረጃ እድገት ወደ ከፍተኛ የሥራ ቦታ ለሚመደብ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜ አይኖርም፡፡ 

12.5. አሠሪው ለክፍት የሥራ መደቡ ከድርጅቱ ውስጥ ብቁ ሠራተኛ ካጣ ከውጭ አዲስ ሠራተኛ ይቀጥራል፡፡ 

12.6. የደረጃ እድገት አፈጻጸሙ በጾታ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወዘተ ልዩነት ሳይደረግበት በትክክል ይሰራበታል፡፡ 

12.7. አሠሪው በሚቋ ቁመው የደረጃ እድገት ኮሚቴ በሚቀርበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ዋና ስራ አስኪያጅ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ የደረጃ እድገቱም ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ይፀናል፡፡ 

12.8. የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ አባላት 

12.8.1. በሰው ሀብት ልማት ዋና ክፍል ኃላፊ የወከለ ሰብሳቢ 

12.8.2. የደረጃ እድገት የሚሰጥበት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወይም አገልግሎት ኃላፊ አባል፡፡ 

12.8.3. የሠራተኛ ማህበር ተወካይ አባል በቁጥር 2

12.8.4. ድርጅቱ የሚወክለው ፀሃፊ ድምጽ አልባ አንድ ሰው 

12.9. የደረጃ እድገት መወዳደሪያ በሚከተለው መሠረት ይሆናል፡፡  

ሀ. ለአገልግሎት 20 ነጥብ 

ለ. የተግባር/ ፈተና 30 ሆኖ የተግባር /የጽሁፍ/ ፈተና ሲሰጥ ተወዳዳሪው ለሚቀጥለው ወድድር ለመቅረብ ቢያንስ የማለፊያውን ነጥብ 60/100 ማግኘት አለበት፡፡ 

ሐ. ሥራ አፈጻጸም 15 ሆኖ ለመወዳደር ሁለት ተከታታይ የሥራ አፈጻጸም ውጤት 2.5 ወደ 3 እንዲሻሻል መሆን አለበት፡፡ የትምህርት ደረጃ 2.5 ወደ 3 እንዲሻሻል 

ሠ. የግል ማህደር 10 

12.10. አንድ ሠራተኛ ለድርጅቱ እድገት መወዳደር የሚችለው በድርጅቱ ውስጥ ቢያንስ የአንድ ዓመት አገልግሎት ከሰጠ በኃላ ነው፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በመመሪያው መሰረት ይሆናል፡፡  

አንቀጽ አስራ ሶስት

ዝውውር 

13.1. ድርጅቱ ሠራተኞችን ከአንድ የሥራ ክፍል ወደ ሌላ የሥራ ክፍል ሊያዘዋውር የሚችለው በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ ሆኖ ዝውውሩም ሠራተኛው በአዋጅና በህብረት ስምምነት ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም የማይነካ ካልሆነ ብቻ ነው፡፡ 

13.2. አንድ ሠራተኛ በህመም ምክንያት በሥራ ውል ከተመለከተው የተለየ ሥራ እንዲሠራ ሀኪም ሲያዝ ድርጅቱ ወደ ሌላ የሥራ መደብ አዛውሮ ይሰራል፡፡ 

13.3. ነፍሰጡር ሴት የምትሰራበት ሥራ ለጤናዋ የማያመች መሆኑ በሃኪም ሲረጋገጥ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 87 እና 88 መሠረት ይፈጸማል፡፡ 

13.4. ድርጅት በአንድ የሥራ ክፍል ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖረውና ማዘዋወሩ ለሥራው የሚጠቅም መሆኑን ሲያምንበት የሠራተኛውን ደረጃ ደመወዝና ጥቅም ሳይቀንስ ወደ ሌላ የሥራ ክፍል አዛውሮ ሊያሰራ ይችላል፡፡ 

አንቀጽ አስራ አራት 

ሥልጠና 

14.1. ድርጅቱ በሚያዘጋጀው የሥልጠና ፕሮግራሞች ላይ እንዲካፈል ለተመረጠው ሠራተኛ የሠው ሀብት ልማት ዋና ክፍል አስፈላጊውን ይፈጽማል፡፡ 

14.2. በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም በሠራተኞች ማህበር በሚዘጋጅ የሞያ ትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የድርጅቱ ሠራተኞች ተካፋይ እንዲሆኑ በሚጠየቅበት ጊዜ ድርጅቱ ይተባበራል፡፡ 

14.3. ማንኛውንም ሥልጠና የወሰደ ሰራተኛ በሰለጠነበት ሙያ ለተወሰነ ጊዜ ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት ለድርጅቱ መሰጠት ግዴታ መግባት አለበት፡፡ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል፡፡ 

14.4. ማንኛውም ሠራተኛ ሥልጠና ከመወሰዱ በፊት ለድርጅቱ የውዴታ ግዴታ መግባት ይኖርበታል፡፡ 

አንቀጽ አስራ አምስት

የሠራተኞች ጤንነትና ደህንነትና ጥበቃ

15.1. ድርጅቱ ሥራ ላይ አደጋ እንዲሁም የጤንነት ጠንቅ የሆነ በሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡

15.2. እንደ ስራው ሁኔታ በሚፈለገው መጠን እየታየ አሰሪው የአደጋ መከላከያዎችን ያቀርባል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ስድስት 

ፍሬያማነት 

16.1. አሠሪውና የሠራተኛው ማህበር በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የሥራ ቅልጥፍና እንዲሁም ጥሩ የሥራ ውጤት እንዲገኝ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ 

16.2. በሠራተኛ ላይ የውድድርና የሥራ ፍላጎት መንፈስ እንዲዳብር በስራቸው ብልጫ የሚያሳዩ ሠራተኞችን አሰሪው ያበረታታል፡፡ በውጤት ላይ የተመረኮዘ የማበረታቻ ሥርዓትም ተግባራዊ ለማድረግ ከማህበሩ ጋር በመተሳሰር ይሠራል፡፡  

የሙከራ ጊዜ ገደብ ከተፈጸመበት ጊዜ ገደብ ከተፈጸመበት ጊዜ ገደብ ጀምሮ በቋሚነት እንደተቀጠረ ይቆጠራል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ሰባት

የምስክር ወረቀት

17.1. አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉን ሲያቋርጥ ድርጅቱ የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል፡፡ 

17.2. የምስክር ወረቀቱ ቀጥሎ የተመለከቱትን ነጥቦች ይይዛል፡፡ 


ሀ. የሠራተኛውን ስም  መ. የአገልግሎት ዘመን 

ለ. የሥራውን ዓይነት  ሠ. የሚያገኘው ደመወዝ 

ሐ. የሥራ ቦታው  ረ. ሥራ የለቀቀበት ምክንያት


በተጨማሪም በድርጅቱ ውስጥ ሲያገለግል ከደመወዝ የከፈለው ታክስና ከደመወዙ የተቀነሰ የጡረታ መዋቾ ተቀንሶ ይጻፍለታል፡፡ 

17.3. የሚሰጠው የምስክር ወረቀቱን የተሰናባቹ ፎቶግራፍ የተለጠፈበትና የድርጅቱ ማህተም የታተመበትን መሆን አለበት፡፡ 

17.4. ማንኛውም ሠራተኛ የምስክር ወረቀቱን ከመውሰዱ በፊት የድርጅቱን ንብረትና ሰነድ መመለስ አለበት፡፡ 

17.5. በሥራ ላይ እያለ የአገልግሎት ማስረጃ ደእንዲጻፍለት የሚጠይቅ ሠራተኛ በንዑስ አንቀጽ 2 በተገለፀው መሠረት የአገልግሎት ማስረጃ የምስክር ወረቀት በዓመት ከሁለት ጊዜ ሳይበልጥ ተጽፎ ሊሰጠው ይችላሉ፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት

ሙከራ ጊዜ

18.1. ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኛ ለ45 ቀን የሙከራ ቀን የሙከራ ጊዜ ይቀጠራል፡፡ ሆኖም ሙከራ ጊዜው ከ45 ተከታታይ ቀናት ሊበልጥ አይችልም፡፡ 

18.2. የሠራተኛው የሙከራ ጊዜ መጨረሻ ከመጠናቀቁ በፊት በአሰሪው አስተያየት ሥራው አጥጋቢ ከሆነ በውሉ መሠረት በቋሚነት የተቀጠረ መሆኑ በጽሁፍ ይረጋገጣል ይህ ካልተገለፀለት የሙከራው ጊዜ ገደብ ከተፈጸመበት ጊዜ ገደብ ጀምሮ በቋሚነት እንደተቀጠረ ይቆጠራል፡፡ 

18.3. በሙከራ ጊዜ ውስጥ ሁለቱም ወገን የቅጥሩን ውል ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ 

ስለ ሥራ ስንብትንና ካሳ ክፍያ 

በስራ ስንብት ምክንያት የሚኖሩ ክፍያዎች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 39፣40 እና 41 እና በተሻሻለው አዋጅ 494 በተደነገገው መሰረት ይከናወናል፡፡ መደበኛ የሥራ ሰዓት 8 ሰዓት በሳምንት እስከ 48 ሰዓት ነው፡፡ ፋብሪካው በምርቱ ሥራና ምርቱን ለሽያጭ ማቅረብ እንዲቸችል የሥራ ሰዓቱን አመቺ በሆነ መንገድ ለማቀድ ሥራውን የሚጀምርበትን፣ የሚያልቅበትን ለመቀየስና የሥራ ሰዓት ለመቀያየር የሰራተኛውንም መብት ሳይነካ የአስተዳደሩ መብት ነው፡፡ ማህበሩ በቅድሚያ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡ 



  1. በፋብሪካው ልዩ ልዩ ዘርፎች የመግቢያና መውጫ የሥራ ሰዓት ዝርዝር ሰንጠረዥ 

ሀ. በምርትና የቢሮ ሥራ ላይ የሚሰሩ ሠራተኞች ከሰኞ እስከ አርብ የመውጫና መግቢያ ሰዓቶች 

ጠዋት

ሥራ መጀመሪያ  የምሳ ሰዓት    ከምሳ በኋላ  መውጫ ሰዓት

2፡00  6፡15  7፡00  10፡50 

ለ. ቅድሜ  የእረፍት ሰዓት  ከእረፍት መልስ  ከሥራ መውጫ 

2፡00  6፡30 4፡40  7፡40 

ሐ.ሱቆች እንዳመቺነት የሥራ ሰዓት ይዘጋጅለታል 

መግቢያ ሰዓት  መውጫ ሰዓት  መግቢያ ሰዓት  ከሥራ መውጫ 

3፡00  7፡00  8፡00 12፡00 

በሥራ መሃከል የእረፍት ጊዜ አስፈላጊነት ቀርቦ ውድቅ ተደርጓል 

መ. ለዘበኛና ለጽዳት ሠራተኞች በቀን ከ8ሰዓት በሳምንት ከ48ሰዓት የማይበልጥ ሆኖ አስተዳደሩ በሚያዘጋጅላቸው የፈረቃ ፕሮግራም መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

  1. ማንኛውም ሠራተኛ ጠዋት ሲገባ እና ከምሳ በኋላ ስራ ሲገባ ይፈርማል፡፡ 

አንቀጽ ሃያ አንድ

ስለ ትርፍ ሰዓት ሥራና ክፍያ

21.1. በዚህ ህብረት ስምምነት አንቀጽ 20 መሰረት ከተወሰነው የቀኑ መደበኛ የሥራ ሰዓት በላይ የሚሰራ ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደሆነ ይቆጠራል አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 67 እና 68 መሰረት ይፈጸማል፡፡ 

21.2. የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚሠራ ሠራተኛ የሚያገኘው ክፍያ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 68 መሰረት ይሆናል፡፡ 

አንቀጽ ሃያ ሁለት 

የሳምንት የእረፍት ጊዜ  

  • ማንኛውም ሠራተኛ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 69 እና 70 መሠረት በ7 ቀናት ውስጥ ያልተቆራረጠ ከ24 ሰዓት የማያንስ የሣምንት እረፍት ያገኛል፡፡ 



አንቀጽ ሃያ ሶስት 

የሕዝብ በዓላት 

አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የሚከበሩ የሕዝብ በዓላት ደመወዝ የሚከፈልባቸው ይሆናሉ፡፡  

አንቀጽ ሃያ አራት

ስለ ፈቃድ

  1. የዓመት እረፍት ፈቃድ 

የድርጅቱ ሠራተኛ ሳይከፋፈል የሚሰጥ የዓመት ፈቃድ ከክፍያ ጋር እንደሚከተለው ይገኛል፡፡ 

  1. አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ 14 የሥራ ቀን የዓመ
    ት ፈቃደ ያገኛል፡፡ 
  2. ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ በተራ ቁጥር 1 በተሰጠው ቀን ላይ በተጨማሪ ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዘመን አንድ የሥራ ቀን ይታከልለታል፡፡ 
  3. የዓመት እረፍት ፈቃድ በሚሰጥበት ጊዜ አሠሪውንና የሠራተኛውን ጥቅም በማስማማትና በማስጠበቅ ምቹ የሆነውን ጊዜ በመምረጥ ነው፡፡ 
  4. በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 76 እና 77 መሰረት ከተፈቀደው ውጪ የዓመት እረፍት ፍቃድ በገንዘብ መለወጥ ይችላል፡፡ አንድ ሰራተኛ የአመት ፈቃድ ሲወስድ ደመወዙ በቅድሚያ ይከፈለዋል፡፡ 
  5. የዓመት ፈቃድ ሊከፋፈል ወይም ሊተላለፍ የሚችለው በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 79 መሰረት ነው፡፡ 
  6. ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተመለከተው መሠረት የተላለፈ ወይም የተቋረጠ የዓመት ፈቃድ ከሚጥለው ሁለት ዓመት በላይ ሊራዘም አይችልም፡፡ 
  7. እረፍት የሚያበቃበትን ጊዜ እጅግ ቢያንስ ከ10 ቀን በፊት ለሰራተኛው መነገር አለበት፡፡ 
  8. የአመት እረፍት ፈቃድ በወር አንድ ጊዜ ከ3 ያልበለጠ እንደ ችግሩ መጠን ይወስዳል፡፡ 
  9. የዓመት እረፍት ፈቃድ አወጣጥ ፕሮግራም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 78 መሠረት ይሆናል፡፡ 
    1. ልዩ ፈቃድ 

    ሀ. ጋብቻና ችግር ሲያጋጥም የሚሰጥ ፈቃድ 

    ሠራተኛ ህጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም ከክፍያ ጋር ለ3 የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ እንዲሁም ሠራተኛ በድንገት ለሚገጥመው ችግር ወይም ሁኔታ ደመወዝ የማይከፈልበት እስከ 10 ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

    ለ. ለማህበር ሥራ የሚሰጥ ፈቃድ 

    የሠራተኞች ማህበር መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ የህብረት ስምምነት ለመደራደር በማህበሩ ስብሰባ ለመገኘት በሴሚናሮች በሥልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ከክፍያ ጋር ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ ይኸውም ሥራውን በማይበድል ሁኔታ በቅድሚያ ለአሰሪው አሳውቆ አሠሪው ሁኔታዎችን ገምግሞ ፈቃድ ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ 

    ሐ. ልዩ ተግባሮች ለማከናወን ለሠራተኛው የሚሰጥ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 83 መሠረት ፈቅዷል፡፡ 

    መ. በትምህርት ክትትል ድርጅቱ ልዩ እገዛ ወይም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 

    ሠ. ተጠቃሚው ሠራተኛ ዋስትና ለድርጅቱ 

    1. ስለማስታወቂያ 

    በአንቀጽ 24 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ፈቃድ ለመውሰድ የሚፈልግ ሠራተኛ በቅድሚያ ለአሰሪው ማስታወቅና ፈቃድ ማግኘቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ 

    አንቀጽ 25 

    የህክምና ፈቃድ 

    1. የህክምና ፈቃድ ጊዜ 
    1. አንድ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ በስራ ላይ በሚደርስበት ጉዳት ሳይሆን በሌላ ህመም ምክንያት ሥራ ለመሥራት ካልቻለ በዚህ አንቀጽ መሰረት የህመም ፈቃድ ያገኛል፡፡ 
    2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ/1/ የተመለከተው ፈቃድ ህመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው 112 ወር ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት ቢወስድም በማንኛውም ሁኔታ ከስድስት ወር አይበልጥም፡፡ 
    3. ማንኛውም ሠራተኛ በህመም ምክንያት ከሥራ ሲቀር አሠሪው ስለሁኔታው ሊያውቅ የሚል ወይም ሠራተኛው ለማስታወቅ የማይችል ካልሆነ በቀር በማግሥቱ ለአሰሪው ያሳውቃል፡፡ 
    4. ማንኛውም ሠራተኛ የህመም ፈቃድ የሚያገኘው በመንግስት የህክምና ድርጅት እና በሪፈር ወደ ግል ህክምና ተገቢ የሆነ የህክምና ወረቀት ሲያቀርብ ነው፡፡ 
    5. ስለ ክፍያ 
    6. በአንቀጽ 25.1 የተጠቀሰው የህመም ፈቃድ ቀጥሎ በተመለከተው ሁኔታ ይሰጣል፡፡ 
    1. ለመጀመሪያ ወር ከሙሉ ደመወዝ ክፍያ ጋር 100 ፐርሰንት 
    2. ለሚቀጥለው ሁለት ወራት ከደመወዝ ሃምሳ በመቶ ክፍያ ጋር 50 ፐርሰንት 
    3. ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ያለ ክፍያ በነጻ 
    1. በዓመት እረፍት ላይ ያለ ሠራተኛ ታሞ ሆስፒታል ሲገባ በሆስፒታል ውስጥ የቆየበትን ከዓመት ፈቃድ ላይ መቀነስ የለበትም፡፡ 

    አንቀጽ ሃያ ስድስት

    የወሊድ ፈቃድ

    26.1. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ምርመራ እንድታደርግ ሀኪም ሲያዝ በሚቀርበው ማስረጃ መሰረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣል፡፡  

    26.2. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት መውለጃዋ ሲደርስ 30 ተከታታይ ወሊድ ፈቃድ እንዲሁም ከወለደች ቀን ጀምሮ 60 ተከታታይ ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣታል፡፡ 

    26.3. ነፍሰ ጡር የሆነች ሰራተኛ ከመውለዷ በፊት ወይም በወሊድ ፈቃድ ላይ እያለች እንደሌላው በሽታ ተቆጥሮ የወሊድ ፈቃድ በማራዘም ከስራ ጋር ግንኙነት ለሌላው በሽታ የሚከፈለው ይከፈላታል፡፡ 

    26.4. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ለመውለድ በተቃረበችበት ጊጊ የተመደበችበት ሥራ በእርግዝና ምክንየት ለማከናወን ባትችል ከሀኪም በሚቀርበው ማስረጃ መሰረት ድርጅቱ ወይም አሠሪ ቀላል ነው ብሎ በሚገምትበት ቦታ ሊያሰራት ይችላል፡፡ 

    26.5. ማንኛውም ነፍጡር የሆነች 

    ሀ. ከመወለዷ በፊት ለምትወስደው የ30 ቀን እረፍት 

    ለ. ከወለደች በኋላ ለምትወስደው የ60 ቀን እረፍት ደመወዝ በቅድሚያ ይከፈላታል፡፡ 

    ሐ. የድርጅቱ ሠራተኛ ያረገዘችው ጽንሰ ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው አደጋ ምክንያት የተጠናወታት /ያስወረዳት/ መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ ለሌሎች አደጋ ለደረሰባቸው እንደሚደረገው በኢንሹራንስ ውል መሰረት ይፈፀማል፡፡ 

    መ. የድርጅቱ ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከሥራ ውጭ በጤንነት ጉድለትና በአንዳንድ እክል ምክንያት ያስወረዳት /የተጠናወታት/ እንደሆነና በሐኪም ተረጋግጦ ፈቃድ የተሰጣት እንደሆነ በአንቀጽ 26 በተመለከተው መሠረት የህመም ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ከ7 ወር በላይ ለሆነ ውርጃ ከሆነና በሐኪም ከተረጋገጠ የአንድ ወር የወሊድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር ታገኛለች፡፡ 

    1. ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር እረፍት ይሰጣታል፡፡ 
    2. አጠቃላይ የወሊድ ፈቃድ አወሳሰድ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 88 መሰረት ይፈጸማል፡፡ 

      አንቀጽ ሃያ ሰባት

      የሐዘን ፈቃድ

      1. የሠራተኛው የትዳርጓደኛ አባት እናት ልጅ የልጅ ልጅ አያት ወንድም እህት ወይም የባል ወይም የሚስት አባት እናት ልጅ የልጅ ልጅ ወንድም እህት አያት ሲሞትበት ከክፍያ ጋር የሶስት የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 
      2. የሠራተኛው አክስት አጎት የእህት ልጅ የወንድም ልጅ ሲሞት ሁለት ቀን ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣል፡፡ 
      3. አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሠራተኛው የሞተበት ዘመድ ስለመሞቱ ማስረጃ አቅርብ ሲባል ማቅረብ አለበት፡፡ 
      4. ሠራተኛው በሀዘን ላይ እያለ ልዩና አሳሳቢ ሁኔታ ቢያጋጥመው የዓመት ፈቃድ ከሌላው ደመወዝ የማይከፈልበት ለ5 (አምስት) ቀን ፈቃድ ይሰጣል፡፡ 
      5. በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው የሠራተኛው ዘመዶች ከአዲስ አበባ ውጭ የሞተበት እንደሆነ እንደቦታው ርቀት እስከ 10 ቀን ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ 
      6. የሠራተኛው ቤተሰብ ሲሞት ድርጅቱን በመወከል ከ5 ያልበለጡ ሰዎች ምርትን በማይጎዳ ሁኔታ ለቀብር በማህበሩ አማካኝነት ይላካሉ፡፡ 

      አንቀጽ ሃያ ስምንት

      በሥራ ስለሚመጡ ጉዳቶች

      1. ሀ. በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት 

      ለ. በሥራ ላይ የደረሰ አደጋ 

      ሐ. በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ የሚባሉት ጉዳዩ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 95/2 እና 98/1 የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 

      1. ከስራ ግንኙነት ያለው አደጋ ወይም ህመም ሲደርስ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 መሰረት ይፈጸማል፡፡     
      2. በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ ወዲያውኑ ለቅርብ አለቃው ወይም ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ ማሳወቅ አለበት፡፡ 
      3. ቀንም ሆነ ማታ በሚሰራ ሠራተኛ ላይ ጉዳት ሲደርስ የመጀመሪያ የህመምና እርዳታ ተደርጎለት ይህ በቂ ሆኖ ካልተገኘ ወዲያውኑ በአሰሪውና ወደ ከፍተኛ ህክምና ይላካል፡፡ 
      4. ሠራተኛው በሥራ ምክንያት በመጣ ጉዳት የሞተ እንደሆነ ለህጋዊ ወራሾቹ የሚሰጠው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110፣ 111፣ 112 መሰረት ይሆናል፡፡ 
      5. የአካል ጉዳት መጠን የሚወስነው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 102 በተመለከተው መሰረት ሚኒስቴሩ በሚያወጣው ሰንጠረዥ መሰረት በሀኪሞች ቦርድ ነው፡፡ 
      6. በጥሬ ገንዘብ ስለሚደረግ ክፍያ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 107 እስከ 109 በተመለከተው መሰረት ፋብሪካው ከመድን ድርጅት ጋር ባደረገው የዋስትና ወይም በመንግስት የጡረታ አዋጅ ቁጥር 715 2003 መሰረት አስፈላጊውን ክፍያ ባደረገው የዋስትና ወይም በመንግስት የጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2008ዓ.ም መሰረት አስፈላጊውን ክፍያ ለራሱ ለሠራተኛው ጥገኞቹ ይከፍላል፡፡ 
      7. የሠራተኛው ጥገኞች ተብለው የሚጠሩት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 110 እና የግል ድርጅት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 715/2003 መሰረት የሟች ህጋዊ ባል ወይም ሚስት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሟች ልጆች ወይም በሟች የሚደገፍ ወላጆች ናቸው፡፡ 

      አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ

      የሕክምና አገልግሎት

      1. ፋብሪካው ለሠራተኛው ጤና አጠባበቅ ይረዳ ዘንድ በጤና ጥበቃ ህግ መሰረት ባሉት የህክምና ባለሙያዎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ነርስ/ ጤና ረዳት 
      2. የክሊኒኩ ነርስ በሚያቀርበው ሀሳብ መሰረት በፋብሪካው ክሊኒክ ደረጃ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ 
      3. ለህክምና ወይም ለምርመራ ሠራተኛው ቀርቦ አገልግሎት የሚሰጥበትን /የሚያበቃበትን/ እለትና ሰዓት የፋብሪካው ክሊኒክ ፕሮግራም ይሰጣል፡፡ 
      4. ወደ ክሊኒኩ ለህክምና የሚላኩ ሰራተኞች ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀው ቅጽ በቅርብ አለቃቸው እየተሞላ ይላካል፡፡ 
      5. ክሊኒኩ ለሠራተኛው የህክምና ፈቃድ ሲሰጥ ወይም ሠራተኛውን ወደ ሆስፒታል ሲልክ ለቅርብ አለቃውና ለሰዓት ቁጥጥር ሠራተኛው ማሳወቅ አለበት፡፡ በሽታው ከአቅም በላይ ከሆነ ክሊኒኩ ያሳውቃል፡፡ 
      6. ድርጅቱ በህክምና ባለሙያዎች ሥራ ላይ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጣልቃ በመግባት በሙያቸው ላይ ተጽዕኖ አያደርግም፡፡ 
      7. በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክሊኒኩ ሁሉምም ሠራተኞች በእኩል ዓይን በመመልከት ያለማዳላት በተሰለፈበት ሞያ ቀቢ አገልግሎት ሠራተኛው ሁሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ 
      8. ድርጅቱ ወይም አሰሪው ለሠራተኛው የህክምና ወጭ 60 ፐርሰንት ዋጋ ይከፍላል፡፡ የሕክምና ወጪው ለሽፍን የሚችለው ድርጅቱ ወደ መንግስታዊ የህክምና ተቋም ሰራተኛውን ከላከ በኋላ መንግስታዊ ተቋሙን ጨምሮ ወደ ግል የህክምና ተቋም ከላከበት ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ የመጣ ማስረጃን ወይም ከራሱ ከመንግስት ተቋም ያመጣ ማስረጃ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ 
      9. ማንኛውንም ሠራተኛ በስራው ላይ እንዳለ ቢታመም የፋብሪካው ክሊኒክ ከሙያ አቅም በላይ ሆኖ ለከፍተኛ ህክምና ሳይልከው በራሱ ፈቃድ ወደ ሌላ ሀኪም ቤት ሄዶ መታከም አይፈቀድም፡፡ ታክሞ ቢገኝ የህክምናውን ወጭ ፋብሪካው አይሸፍንም ወይም አይቀበልም፡፡ ከሥራ የቀረበትም ቀን እንደ ቀሪ ተቆጥሮ የሥነ ሥርዓት ጉድለት እርምጃ ይወስዳል፡፡ ሆኖም ግን ከስራ ሰዓትና ቀናት ውጪ ሰራተኛው ከታመመ በሚያርበው ማስረጃ መሠረት በተራ ቁጥር 8 ይ የተሰጠው መሰረት ይስተናገዳል፡፡ 
      10. ከሥራ ሰዓት ውጪ ለሚደርስበት ድንገተኛ ህመም በመንግስት የህክምና ተቋም ማስረጃ ካመጣ ወጭው በህብረት ስምምነቱ መሰረት ይሸፈናል፡፡ 
      11. ፋብሪካው እንደአስፈላጊነቱ ለሠራተኛው የተላለፊ በሽታ መከላከያ ክትባት ይሰጣል፡፡ ሰራተኛውም ክትባቱን የመከተብ ግዴታ አለበት፡፡ ፈቃደኛ ካልሆነ እስኪከተብ ከሥራ ይታገዳል፡፡ 
      12. ሠራተኛው ሀኪም የሠጠውን የህክምና ትዕዛዝ ባለመቀበል ለሚደርስበት ጉደት ፋብሪካው ኃላፊ አይሆንም፡፡ 
      13. የኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ተጠያቂዎች እድልዎና መገለል እንዳይደርስባቸው ያደርጋል፡፡ በጋራ የመከላከል ስልትም ይነድፋል፡፡ 
      14. ሠራተኛው ከታወቀ የመንግስት የዓይን ሕክምና መነጽር እንደገዛ ሲታዘዝለት ድርጅቱ የመነፅሩን ዋጋ 60% ይሸፍናል፡፡ 

        አንቀጽ ሰላሳ

        የአደጋ መከላከያ የደንብ ልብስ 

        1. በሠራተኛው ላይ በሥራ ቦታ አደጋ እንዳይደርስበትና ከሥራ ጋር ግንኙነት ባለው አደጋ ሲሆን ሠራተኛውም ድርጅቱ ወይም አሰሪው የሚሰጠውን የአደጋ መከላከያና የደንብ ልብስ በጥንቃቄ በሥራ ጊዜ ብቻ መገልገል ግዴታው ነው፡፡ 
        2. በየክፍሉ ሊሰጥ የሚገባው የደንብ ልብስና መከላከያዎች 
        1. ለቆረጣ ኃላፊ ለቆረጣ ሱርቫይዘር በስድስት ወር አንድ ጊዜ አንድ ካኪ ካፖርትና አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ ቆዳ ጫማ ይሰጣል፡፡ 
        2. ለጨርቅ ቆራጭ፣ ለርሳስ፣ ለቆራጭ ረዳት በዓመት አንድ ካኪ ካፖርት በስድስት ወር አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ የቡናኝ መከላከያና የእጅ ጓንት 
        3. ለቁጥጥር ሰጭና አከፋፋይ 
        4. በስድስት ወር አንድ ካኪ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 
        1. ለግምጃ ቤት ሠራተኛ 
        1. ለመጋዘን ኃላፊዎች ሠራተኞች እንዲሁም ለጉልበት ሠራተኞች በስድስት ወር አንድ ካኪ ካፖርት ይሠጣል፡፡ አንድ ቆዳ የአገር ውስጥ ጫማ ይሰጣል፡፡ 
        2. ለጉልበት ሠራተኞች በተጨማሪ በወር አንድ ጊዜ አንድ የልብስ ሳሙና ይሰጣል፡፡ 
        1. ለቴክኒክ አገልግሎት ኃላፊ 
        1. ለቴክኒክ አገልግሎት ኃላፊ 

        በስድስት ወር አንድ ካኪ ካፖርት በዓመት አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ ቆዳ ጫማ ይሰጣል፡፡ 

        1. ለመካኒኮች፣ ለኤሌትሪክሻያኖችና ኦይለር በዓመት አንድ ካኪ ካፖርትና ቱታ አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ ቆዳ ጫማ ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በወር አንድ ሳሙና ይሰጣል በጋራ የሚያገለግሉ የፍንጣሪ መከላከያ መነጽር፣ የቆዳና የፕላስቲክ የእጅ ጓንት ይዘጋጃል፡፡ 
        2. ለቴክኒክ ፀሃፊ /ለምርት ፀሃፊ/ ለምርት ክትትል ኃላፊ በዓመት አንድ ካኪ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 
        1. ለቢሮ ተላላኪዎች /ለጽዳት ሠራተኞች/
        1. ለሴቶች ጽዳት ሠራተኞች
        1. ለጥበቃ ኃላፊና ጥበቃ ሠራተኞች 
        1. በዓመት አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ ቆዳ የሥራ ጫማ ፖሊስተር ካኪ የሆነ አንድ ጉርድ ቀሚስ ኮትና መለዩ ወይም ኮት ሱሪና መለዩ እንዲሁም ድርጅቱ ከሚያመርተው የአገር ውስጥ ጨርቅ አንደኛ ደረጃ የተመረተ ሸሚዝ ይሰጣል፡፡ 
        2. በ3ዓመት እንድ ጊዜ ለብርድ መከላከያ የሚሆን የሱፍ ካፖርትና የዝናብ ልብስ ይሰጣል፡፡ 
        1. ለሽያጭ ሰራተኞች አንድና ሁለት ጉርድ ቀሚስና ኮት ፖሊስተር ካኪና ሸሚዝ ድርጅቱ
        2. ከሚያመርተው የአገር ውስጥ የሸሚዝ ጨርቅ አንደኛ ደረጃ የተመረተ እንዲሁም አንድ ጥንድ የአገር ውስጥ ጫማ ይሰጣል፡፡ 
        3. ለልብስ ሰፊዎች ለልብስ ተኳሾች ክር ቆራጮችና አጣፊዎች በዓመት አንድ የሥራ ልብስ ይሰጣል፡፡ 
        4. ለመዝገብ ቤት ሰራተኛና ሰዓት ተቆጣጣሪ 

        በዓመት አንድ ካኪ የሥራ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 

        1. ለዲዛይን ቤት አገልግሎት ኃላፊና ዲዛይነር 
        1. ለዲዛይነር አገልግሎት ኃላፊ 

        በዓመት አንድ የሥራ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 

        1. ለዲዛይነር 

        በዓመት አንድ የሥራ ካፖርት ይሰጣል፡፡  

        1. ለነርስና ጤና ረዳት
        1. ነርስ 

        በዓመት አንድ ነጭ ቴትሮን የሥራ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 

        1. ለጤና ረዳት 

        በዓመት አንድ ፖሊስተር ካኪ የሥራ ካፖርት ይሰጣል፡፡ 

        አንቀጽ ሰላሳ አንድ

        የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም

        ማንኛውም ድርጅቱ ሰራተኛ በአደጋ ወይም በህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ቢለይ 

        1. በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ማህበሩ በሚያቀናጀው መሰረት ስራውን በሚጎዳ መልኩ የድርጊቱ ሰራተኛ እንዲገኙ ያደርጋል ተሽከርካሪ ይመደባል፡፡ 
        2. ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈፀሚያ 1,000.00 አንድ መቶ ሺ ብር ከድርጅቱ ወጪ በማህበሩ አማካኝነት ለሟች የቅርብ ተጠሪ ይከፈላል፡፡ 
        3. ለድርጅቱ ስራ ጉዳይ ታዞ ወይም ለሙያ ስልጠና ተልኮ የሞተ አደጋ ለደረሰበት ሰራተኛ በውጭ አገርም ሆነ በአገሩ ውስጥ ከሞተበት ቦታ ወደ ቤቱ ለመጓጓዝ የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ 




          አንቀጽ ሰላሳ ሁለት

          የደመወዝ ጭማሪ

          1. ድርጅቱ በብር1.5 እና ከኦዲት በኋላ የተጣራ ትርፍ ካገኘ በደመወዝ ስኬል መሰረት የአንድ እርከን ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሬ ያደርጋል፡፡ 
          2. የደመወዝ ጭማሪ የሚያደርገው በድርጅቱ ቢያንስ ቢያንስ አንድ ዓመት ላገለገለ ሠራተኛ ብቻ ነው፡፡ 
          3. የደመወዝ ጭማሪ ማግኘት የማይቻል ከሆነ ጉርሻ ይሰጣል፡፡  

          አንቀጽ ሰላሳ ሶስት 

          ጉርሻ 

          ፋብሪካው /ድርጅቱ/ ማህበሩ በእያንዳንዱ በጀት ዓመት ሥራውን ለማከናወን ያወጣውን ማንኛውም ወጭ፣ ለመንግስት መክፈል ያለበት ማንኛውንም ግብርና በዚህ አንቀጽ መሰረት ለሠራተኛው የሚከፈለው ጉርሻ ይሰጣል፡፡  

          33.1. ከብር 1.5 በላይ የተጣራ ትርፍ ካገኘ የአንድ ወር ደመወዝ 

          33.2. ከብር 600000 የተጣራ ትርፍ ካገኘ የአንድ ወር ተኩል ደመወዝ 

          33.3. ከላይ የተጠቀሱት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉት የድርጅቱ ቀጣይ ትርፋማ እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት ይሆናል፡፡  

          33.4. ከብር 1.5 በታች ከተገኘ ለሠራተኛው የሚሰጠው የቦነስ ክፍያ መጠን ድርጅቱ ከታክስ በኋላ ካስመዘገበው የተጣራ ትርፍ 10% ይሆናል፡፡ 

          33.5. የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሁለት ጊዜ የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3 ከዚያ በላይ ከሆነ ቦነስ ይሰጣል፡፡ 

          አንቀጽ ሰላሳ አራት

          የሻይ ቤትና የስፖርት ክበብ

          ድርጅቱ ባለው አቅም ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውል አንድ ሻይ ክበብ ያዘጋጃል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም የሻይ ቤቱ አስተዳደር በድርጅቱ እና በማህበሩ አመራር በኩል ይሆናል፡፡ 

          በኮሚቴው ሲመራ 

          • ከማኔጅመንቱ 
          • ከመ.ሠ.ማህበሩ 
          • ከጠቅላላ ሠራተኛ 


          አንቀጽ ሰላሳ አምስት

          በፍርድ ስለሚታሰሩ ሠራተኞች

          በፍርድ የሚታሰሩ ሠራተኞች ጉዳይ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/በ/መሠረት ይፈጸማል፡፡ በድርጅቱና በማህበሩ ኮሚቴ ግምገማ በሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ መሠረት ይፈጸማል፡፡ 

          አንቀጽ ሰላሳ ስድስት 

          ስለመልእክት   

          1. አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ በቤተሰብ ላይ ችግር መድረሱ ከተነገረ ድርጅቱ መልዕክቱን ለሠራተኛው ያስተላልፋል፡፡ 
          2. በድርጅቱ አድራሻ ለሰራተኞች የሚመጡትን ድብዳቤዎች ተቀብሎ ለሰራተኛው ይሰጣል፡፡ 

          አንቀጽ ሰላሳ ሰባት 

          ልዩ ልዩ ጥቅሞች 

          1. ሰራተኛው የፋብሪካውን ውጤት ለመግዛት ሲፈልግ ድርጅቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ይሸጥለታል፡፡ 
          2. በመደበኛ የስራ ቀን እና በትርፍ ስራ ሰዓት ሲታዘዝ ወደ ስራ ሲገባና ሲወጣ ድርጅቱ ሰርቪስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሰርቪስ አገልግሎት የማያቀርብ ከሆነ ግን ትራንስፖርት ታሪፍ መሰረት ሂሳቡን ይከፍላል፡፡ 
          3. ድርጅቱ በአመት ሁለት ጊዜ እንደሁኔታው እያየ ከድርጅቱ ምርት በዱቤ ለሰራተኛው ይሸጣል፡፡ ከቆረጣ ክፍል የወዳደቁ ትልታይ ጨርቆችና ጨርቅ ተጠቅልሎ ሚጠባቸው ማዳበሪያዎች፣ ቱቦ፣ ጆንያ፣ ወ.ዘ.ተ ለሰራተኛው ማህበሩ እንደ አስፈላጊነቱ በነፃ ይሰጣል፡፡ 
          4. ድርጅቱ በሚያስራቸው ሁሉም ሰራተኛን ይሸፍናል፡፡ 
          5. ግን ድርጅት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ዋስትና ቁጥር 715/2003 ድርጅቱና ማህበሩ በጋራ ይተገበራሉ፡፡ 

          አንቀጽ 38 

          ውሎ አበል 

          አንድ ሰራተኛ ለፋብሪካው /ድርጅቱ/ ስራ ስልጠና ሴሚናር ትእዛዝ ከድርጅቱ ስራ ቦታ ውጭ ተልኮ ሲውልና ሲያድር ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት የውሎ አበል ይከፈለዋል፡፡ 



          ደመወዝ  ቁርስ  ምሳ  እራት  መኝታ  ጠቅላላ 

          10  25  25  40 

          170-1000  5 11 11 23 150.00

          1001-2000  5 12 12 26 160.00

          2001-2000  6 13 13 33 170.00

          3501 - 5000  6 15 15 34 180.00

          5001 - 7500   190.00

          የቁርስ አበል የሚከፈለው የተላከበት ቦታ አዳር ለወጣ ሠራተኛና ከምድብ የስራ ቦታው በስራ መጀመሪያ ከሰዓት የተገኘው ሰራተኛ ነው፡፡ የምሳ አበል የሚከፈለው ጉዞው ተጀመረው ከቀኑ 6፡00ሰዓት በፊት ለተቀሰቀሰ ሰራተኛ ነው፡፡ የእራት አበል የሚከፍለው በተባለበት ቦታ ላደረገ ሰራተኛ ነው፡፡ 

          አበል የሚከፍለው ከድርጅቱ የስራ ቦታ 3.5ኪ.ሜ ርቆ ከሄደ ነው፡፡  

          አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ

          አመታዊ ብድር

          39.1. እያንዳንዱ ሰራተኛ ብድር በፈለገ ጊዜ በቂ ዋስትና ማቅረብ የሚችል የድርጅቱን ሰራተኛ ዋስ በመጥራት በአንድ ዓመት ከፍሎ የጨረሰው የሁለት ወር ደመወዝ በብድር ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም የብድሩ አጠቃላይ መተን ከብር 80.00 ሰማንያ ሺህ ብር አይበልጥም፡፡ 

          39.2. የሰራተኛው ችግር ተመልክቶ ብድር ሚፈቅድ ከድርጅቱና ከሰራተኛው ማህበሩ ተውጣጣ ኮሚቴ ነው፡፡ 

          39.3 ብድር የሚሰጠው ሰራተኛ በድርጅቱ ቢያንስ የአንድ ዓመት አገልግሎት መስጠት አለበት፡፡ 

          አንቀጽ አርባ

          ለጊዜው ስለሚደረግ እገዳ

          እገዳ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 18 መሰረት አለበት 

          አንቀጽ አርባ አንድ

          የስራ ውል ሲቋረጥ ስለሚደረግ ክፍያ

          ስራ ውል ሲቋረጥ ማድረግ ክፍያ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ይሆናል፡፡ 


          አንቀጽ አርባ ሁለት 

          የደመወዝ ቅነሳ 


          ሰራተኛው ደመወዝ መቀነስ የሚቻለው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 59 ተራ 1 እና 2 መሰረት ነው፡፡ 

          አንቀጽ አርባ ሶስት 

          የአደጋ ጊዜ 

          የአደጋ ጊዜ በአሰሪና በሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162 ከ1 እስከ 5 ባለው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡  

          አንቀጽ አርባ አራት 

          ስራ ማቆምና መዝጋት 

          ስራ ማቆምና መዝጋት በአሰሪና በሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 157 እና 158 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡  

          አንቀጽ አርባ አምስት 

          የህጎች አፈፃፀም 

          የህጎች ውጤት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 3777/1996 በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 494/98 በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡ 

          አንቀጽ አርባ ስድስት 

          ስምምነቱን ስራ ላይ ስለማዋልና የሚፀናበት ጊዜ 

          ይህ ህብረት ስምምነት ጸድቆ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተመዘገበበት ወር መጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ2ዓመት ስምምነት ውስጥ የተተቀሱትን ሁሉ አሰሪና ማህበሩ በስራ ላለማዋል ተስማምተናል፡፡ 

          በድርጅቱ በኩል  በሰራተኛ ማኅበር በኩል

          እማኞች በድርጅቱ በኩል  እማኞች በሰራተኛ በኩል 

          1. ______________ 1. ______________
          2. ______________ 2. ______________
          3. ______________ 3. ______________ ቀቀቀቀቀቀ


          Novaster Garment - 2008

          Start date: → 2008-02-01
          End date: → 2010-01-31
          Ratified by: → Ministry
          Name industry: → Manufacturing
          Name industry: → Manufacture of wearing apparel
          Public/private sector: → In the private sector
          Concluded by:
          Name company: →  Novaster Garment
          Names trade unions: →  የኖቫስታር ጋርመንት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል/ማህበር መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር

          TRAINING

          Training programmes: → Yes
          Apprenticeships: → No
          Employer contributes to training fund for employees: → No

          SICKNESS AND DISABILITY

          Provisions regarding return to work after long-term illness, e.g. cancer treatment: → No
          Paid menstruation leave: → No
          Pay in case of disability due to work accident: → Yes

          HEALTH AND SAFETY AND MEDICAL ASSISTANCE

          Medical assistance agreed: → Yes
          Medical assistance for relatives agreed: → No
          Contribution to health insurance agreed: → Yes
          Health insurance for relatives agreed: → No
          Health and safety policy agreed: → Yes
          Health and safety training agreed: → No
          Protective clothing provided: → Yes
          Regular or yearly medical checkup or visits provided by the employer: → No
          Monitoring of musculoskeletal solicitation of workstations, professional risks and/or relationship between work and health: → 
          Funeral assistance: → Yes
          Minimum company contribution to funeral/burial expenses: → ETB 100000.0

          WORK AND FAMILY ARRANGEMENTS

          Maternity paid leave: → 13 weeks
          Maternity paid leave restricted to 100 % of basic wage
          Job security after maternity leave: → No
          Prohibition of discrimination related to maternity: → No
          Prohibition to oblige pregnant or breastfeeding workers to perform dangerous or unhealthy work: → 
          Workplace risk assessment on the safety and health of pregnant or nursing women: → 
          Availability of alternatives to dangerous or unhealthy work for pregnant or breastfeeding workers: → 
          Time off for prenatal medical examinations: → 
          Prohibition of screening for pregnancy before regularising non-standard workers: → 
          Prohibition of screening for pregnancy before promotion: → 
          Facilities for nursing mothers: → No
          Employer-provided childcare facilities: → No
          Employer-subsidized childcare facilities: → No
          Monetary tuition/subsidy for children's education: → No
          Leave duration in days in case of death of a relative: → 3 days

          GENDER EQUALITY ISSUES

          Equal pay for work of equal value: → No
          Discrimination at work clauses: → Yes
          Equal opportunities for promotion for women: → No
          Equal opportunities for training and retraining for women: → No
          Gender equality trade union officer at the workplace: → No
          Clauses on sexual harassment at work: → No
          Clauses on violence at work: → Yes
          Special leave for workers subjected to domestic or intimate partner violence: → No
          Support for women workers with disabilities: → No
          Gender equality monitoring: → No

          EMPLOYMENT CONTRACTS

          Trial period duration: → 45 days
          Part-time workers excluded from any provision: → No
          Provisions about temporary workers: → No
          Apprentices excluded from any provision: → No
          Minijobs/student jobs excluded from any provision: → No

          WORKING HOURS, SCHEDULES AND HOLIDAYS

          Working hours per day: → 8.0
          Working hours per week: → 48.0
          Working days per week: → 6.0
          Paid annual leave: → 14.0 days
          Paid annual leave: → 2.0 weeks
          Rest period of at least one day per week agreed: → Yes
          Provisions on flexible work arrangements: → No

          WAGES

          Wages determined by means of pay scales: → No
          Adjustment for rising costs of living: → 

          Wage increase

          Once only extra payment

          Once only extra payment due to company performance: → Yes

          Premium for overtime work

          Allowance for commuting work

          Meal vouchers

          Meal allowances provided: → No
          Free legal assistance: → No
          Loading...