Ethiopia - Collective Agreements Database


ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ

ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ




የኅብረት ስምምነት









ታህሳስ 2008ዓ.ም

አዲስ አበባ



ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ 

እና ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ የህብረት ስምምነት

ማውጫ

ተ.ቁ 

ርዕስ 

ገጽ

 

1

ትርጉም 

1

የህብረት ስምምነት አላማ 

1-2 

3

የተፈፃሚነት ወሰን 

2-3 

4

ማህበርን ስለማሳወቅ 

3

5

በህብረት ስምምነቱ ውስጥ ስላልተጠቀሱ ጉዳዮችና የህግ ውጤት 

3

6

የስምምነቱ አተረጓጎም 

3

7

የስምምነቱ ወሰን

3-4 

8

ስህተት ስለማረም 

4

9

የሠራተኛ ማህበር በፋብሪካው አስተዳደር ለመካፈል ስለሚችልበት ሁኔታ 

4


ምዕራፍ ሁለት


10

የፋብሪካው መብት 

6-7  

11

የአሰሪው ግዴታ 

7-8

12

ኩባንያው ለሠራተኛ ማህበሩ የሚሰጠው ግልጋሎት 

8

13

የሠራተኛ ማህበሩ መብት 

8-9

14

የሠራተኛ ማህበሩ ግዴታዎች 

9

15

የሠራተኛ መብት 

9-10

16

የሠራተኛ ግዴታዎች 

11-12

17

የሥራ ውል አመሰራረት የሠራተኛ ቅጥር፣ ምደባ፣ ስልጠና፣ ግምገማ፣ ዕድገትና ዝውውር 


18

የሠራተኛ አቀጣጠር ስርዓት 

13-14

19

የሥራ ውል አመሰራረት 

14

ተ.ቁ 

ርዕስ 

ገጽ 

20

የሙከራ ጊዜ 

14

21

ስልጠና 

15

22

የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም ምዘና 

15

23

የደረጃ ዕድገት  

16-17

24

ዝውውር 

17

25

ተተኪ ሠራተኛ ስለመመደብ 

18

26

ስንብት 

18-19

27

የሥራ ሰዓት የህዝብ በዓላት የትርፍ ሰዓትና የሳምንት የዕረፍት ቀን 

19-20

28

የህዝብ በዓላት 

20

29

የትርፍ ሰዓት ሥራ 

20-21

30

ደመወዝና ቅድሚያ ክፍያ 

21

31

የውሎ አበል 

21

32

ለገንዘብ ያዢና ለደመወዝ ክፍያ የሚሰጥ ክፍያ 

21

33

የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት የሚደረግ ክፍያና ካሳ 

22

34

ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ 

22

35

የህክምና አገልግሎ አሰጣጥ 

22

36

ከሥራ ጋር ለተያያዘ ጉዳት የሚሰጥ ህክምና 

23

37

ሴፍቲ ኮሚቴ /ደህንነት/

23

38

ኢንሹራንስ

23-24

39

የጋብቻ ፈቃድ 

24

40

የዓመት ፈቃድ 

24

41

የሐዘን ፈቃድ 

24

42

የወሊድ ፈቃድ 

24

43

ለአጋጣሚ ችግር የሚሰጥ ፈቃድ 

25

44

ለሠራተኛ ማህበር ሥራ የሚሰጥ ፈቃድ 

25

45

ልዩ ልዩ ፈቃዶች 

25

46

የአደጋ መከላከያ፣ የሥራ ልብስና ሳሙና 

25

.

ርዕስ

ገጽ


ምዕራፍ ሶስት


47

የስነ ስርዓት እርምጃ አወሳሰድ 

  1. የቅጣት እርምጃዎችና የአቀጣጥ ሥነስርዓት 
  2. የቅጣት እርምጃ ሥርዓት 
  3. በማስጠንቀቂያ ከሠራ ማሰናበት 
  4. በተለያዩ የዲሲፕሊን ጉዳዮች የሚወሰድ የሥነሥርዓት እርምጃዎች 
  5. ከሠራ ስለማገድ 

26-34

48

የቅሬታ አቀራረብ ሥነስርዓት 

35

49

ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 

35

50

አተረጓጎም 

35

51

ያልተሽፈኑ ጉዳዮች 

35

52 

ማሻሻያ 

35


ምዕራፍ አራት 

36

53 

በሥራ ላይ ማዋል 

36

54

መተካት 

36


  1. በዚህ ኅብረት ስምምነት እና ወደፊት ድርጅቱና ማህበሩ በጋራ በሚስማሙባቸው ጉዳዬች እንዲሁም መንግስት በሚያወጣቸው ሕጎች፣ መመሪያዎችና ደንቦች የሚደነገጉ መብትና ግዴታዎች እንዲከበሩ ማድረግ፣ 
  2. ፋብሪካው ሀገሪቱ በምትመራበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት በነፃ ገበያ ተወዳዳሪ እንደመሆኑ ምርት በጥራት እንዲዘጋጅና የሠራተኛው የምርታማነት ባህል እንዲጎለብት ለማድረግ፣
  3. ድርጅቱና ማህበሩ ለአንድ ዓላማ በመስራ የድርጅቱን ህልዉናና እድገት በማይነካ አኳኋን የሰራተኛው ደህንነት ተጠብቆ የኑሮው ደረጃ እንዲሻሻልነና የሥራ መብቱ እንዲከበር ለማድረግ፣  
  4. የፋብሪካው ጥሬ ዕቃዎች በውጭ ምንዛሬ ከውጭ አገር የሚገኙ እንደመሆናቸው በጥንቃቄ እንዲያዙና ለተፈላጊው አገልግሎ እንዲውሉ ለማድረግ፣
  5. ብኩንነትን በማስወገድ ለፋብሪካው ንብረትና ምርት ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ፣ 
  6. አዳዲስና ዘመናዊ የአሠራር ስልቶችን ሥራ ላይ በማዋል በአነስተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት የሚመረትበትን ሁኔታ በማረጋገጥ የድርጅቱ የሥራ ዕቅድ ግቡን እንዲመታና ከተቻለም ከዕቅድ በላይ እንዲያመርት ለማድረግ፣ 
  7. በፋብሪካው አስተዳደር እና በፋብሪካው ሠራተኞች መካከል ጤናማ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር፣ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍንና የሠራተኛው የሥራ ፍላጎትና የዲስፕሊን ዕውቀት እንዲዳብር ለማድረግ፣ 
  8. የድርጅቱ ህልውናና አቋም እንዲጠናከር ለማድረግ፣ 
  9. የሠራተኞች ጤንነትና ደህንነት መጠበቂያ ዘዴዎችና መሣሪያዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ ለመፈለግ፣ 
  10. የዲስፒሊንና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓትን የሚመለከቱ መመሪያዎች በስርዓት እንዲቀረፁ ለማድረግ፣ 
  11. የድርጅቱ ሠራተኞች ሙያቸውንና እውቀታቸውን የሚያዳብሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፣ 
  12. የሠራተኞች ደመወዝና ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች አከፋፈልን ለመወሰን፣

አንቀጽ ሦስት

የተፈጻሚነት ወሰን

  1. በተለየ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር ይህ የኅብረት ስምምነት በፋብሪካውና በሠራተኛ መካከል በሚደረግ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ውል ግንኙነት ላይ ተፈጻሚነት አለው፡፡  
  2. ሆኖም ይህ ኅብረት ስምምነት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ 

ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ

እና 

ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኛ ማህበር መካከል የተደረገ 

የኅብረት ስምምነት


ምዕራፍ አንድ

አንቀጽ አንድ

ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ፡


  1. “አዋጅ” ማለት የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ማለት ነው፡፡   
  2. “ሕጎች” ወይም “መመሪያዎች” ማለት መንግስት ያወጣቸውንና ወደፊት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና ሕጎች ማለት ነው፡፡ 
  3. “ፋብሪካ” ወይም “ድርጅት” ማለት በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዞንግ ኢት ጨ/ጨ ፋብሪካ ማለት ነው፡፡ 
  4. “የሠራተኛ” ማህበር ማለት ዞንግ ኢት ጨ/ጨ ፋብሪካ መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር ማለት ነው፡፡ 
  5. “የሠራተኛ” ማለት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4 መሠረት ደመወዝ እየተከፈለው በድርጅቱ ላልተወሰነ ወይም ለተወሰነ ጊዜ የጉልበት ወይም የአእምሮ ሥራ ለመስራት ለፋብሪካው ግዴታ የገባ ማለት ነው፡፡ 
  6. “የኅብረት ስምምነት” ማለት በዞንግ ኢት ጨ/ጨ ፋብሪካና መሠረታዊ የሠራተኞች ማህበር መካከል የተደረገ የኅብረት ስምምነት ማለት ነው፡፡ 
  7. “የአስተዳደር ሥራ መመሪያ” ማለት አዋጁንና ኅብረት ስምምነቱን መሠረት በማድረግ በድርጅቱ ተዘጋጅቶና በሥራ አመራር ቦርድ ፀድቆ ተግባራዊ የሚሆን ዝርዝር የአስተዳደር ተግባራትን የያዘ መመሪያ ማለት ነው፡፡ 
  8. “ደመወዝ” ማለት የፋብሪካው ሠራተኛ በቅጥር ውሉ መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ በቀን ወይም በወር ታስቦ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡  

አንቀጽ ሁለት

የኅብረት ስምምነቱ ዓላማ

ይህ የኅብረ ስምምነት የሚከተሉትን ዓላማዎች የያዘ ሲሆን፣ ዓላማውን በተግባር ለመተርጎም ድርጅቱና ማህበሩ ተስማምተዋል፡፡ 


ፋብሪካውና የሠራተኛው ማህበር በመተባበር ይህ የኀብረት ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውልና ተፈፃሚነት እንዲኖረው ተገቢውን ጥረት የማድረግ ግዴታና ኃላፊነት አለባቸው፡፡ 

አንቀጽ ስምንት 

ስህተት ስለማረም 

ፋብሪካው የኅብረት ስምምነቱ የማይፈቅደውን ወይንም በስሌት ስህተት ለሠራተኛው የማይገባ የሥራ ደረጃ፣ የደመወዝ ዕድገት ጭማሪ ወይም ቅናሽ ቢደረግ፣ የዓመት ዕረፍት ፍቃድ ቢሰጥ ይህንንም የመሳሰሉ ሌሎች ስህተቶች ተፈጽመው ሲገኙ እና ሠራተኛው ማግኘት ከሚገባው ጥቅም በላይ ማግኘቱ ሲታወቅ አስተዳደሩ ስህተቱን እንዳወቀው ማረምና ማስተካከል ይችላል፡፡ 

አንቀጽ ዘጠኝ 

የሠራተኛ ማህበር በፋብሪካው አስተዳደር ለመካፈል ስለሚችልበት ሁኔታ

የሠራተኛ ማህበር የፋብሪካውን ሥራ ለማቀላጠፍ ይቻል ዘንድ በሚከተሉት ተግባሮች ሃሳብ በመስጠት ተካፋይ ይሆናል፡፡ 

  1. ፋብሪካው ማህበር የፋብሪካውን ሥራ ለማቀላጠፍ ይቻል ዘንድ በሚከተሉት ተግባሮች ሃሳብ በመስጠት ተካፋይ ይሆናል፡፡ 
  2. ሠራተኞች ለደረጃ ዕድገት ሲወዳደሩ በዚህ ኅብረት ስምምነት መሠረት ማህበሩ የኮሚቴ አባል በማቅረብ በውክልና ተካፋይ ይሆናል፡፡ 
  3. በድርጅቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ላይ ይሳተፋል፡፡ 

ምዕራፍ ሁለት 

አንቀጽ አስር 

የፋብሪካው መብት 

10.1. የፋብሪካውን ሥራ የመምራት፣ የማቀድ፣ የመቆጣጠርና እንዲሁም በዚህ ህብረት ስምምነት በተጠቀሱ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ ሠራተኞችን የመቅጠር በየቦታው የመመደብ የማሳደግና ከቦታ ቦታ ለማዛወር መብቱ የፋብሪካው ነው፡፡ 

10.2. በዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ሠራተኛን በበቂ ምክንያት መቅጣት ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ማድረግና እንዲሁም ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ ሁኔታ ጉዳይ እስከሚጣራ ድረስ በሌላ ስራ ለማሰራት ወይም ማገድ ይችላል፣ ሆኖም ግን ሰራተኛው አጥፊ ካልተገኘ የታገደበት ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ቀድሞ ሥራው ይመልሰወዋል፡፡ 

10.3 አዲስ የሥራ ቦታን መክፈት ወይም ማጠፍ አስፈላጊነቱን የመወሰን በየሥራ መደብ አስፈላጊውን የሰው ኃይል የመወሰን ሠራተኛን የማሳደግ እና የእርከን ጭማሪ የማድረግ ለየሥራ መደቡ የሚፈለገውን ትምህርት ደረጃ የሥራ ልምድ የማውጣት የመወሰን እና ሠራተኛን የመሸለም በህጉ መሠረት አወዳድሮ የመቅጠር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሠራተኛን የመሸለም በሕጉ መሠረት የማዛወር መብት የፋብሪካው ነው፡፡ 

10.4. ስለፋብሪካው የስራ ሁኔታ እና የፋብሪካው ሀብትና ንብረት አጠባበቅ ከሌላ ሶስተኛ ወገን ጋር የመነጋገር፣ ስለዕቃ ግዥና ሽያጭ የመዋዋል ኢንሹራንስ የመግባት ሌላም የፋብሪካው ሥራ አስፈላጊ የሆነ ውል መግባት በፋብሪካው ስም የመክሰስና መክሰስ መብት አለው፡፡ 

10.5. በፋብሪካው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሥራንና የሰራተኛ ጉዳይን በሚመለከት በትምህርት ፕሮግራም በትርፍና ኪሳራ ወይም በማንኛውም ጉዳይ መግለጫ የመስጠትና ማስታወቂያ የማውጣት መብት አለው፡፡ 

10.6. ሠራተኛው ከፋብሪካው የተበደራቸውን ብድሮች የመንግስት ግብር፣ ለመክፈል በጹሁፍ የተስማማበትን ገንዘብ ፋብሪካው ሠራተኛው ከሚያገኘው መደበኛ ደመወዝ ቀንሶ የመተካት ወይም ለህጋዊ ባለመብቶች መክፈል መብት አለው፡፡ 

10.7. በአጥፊዎች ላይ ሊወሰድ የሚገባውን የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች በህጉ መሠረት የመወሰን የማሻሻል ቅጣቶችን የማንሳት ወይም ይቅርታ የማድረግ የሚመለከታቸው የማኔጅመንት አካል መብት ነው፡፡ ሆኖም ከስራ የተሰናበተ ሠራተኛ ይቅርታ ማድረግ የሚችለው የፋብሪካው ዋና ሥራአስኪያጅ ወይም በዋና ሥራ አስኪያጅ የተወከለ ብቻ ነው፡፡ 

10.8. ህግን ደንብንና መመሪያን በመከተል የቅጥር፣ የእድገት፣ የዝውውር፣ የትምህርት ስልጠና እና ሌሎች የሰራተኛውን እንቅስቃሴ የሚመለከትና የምርትና ጥገና የግዥ የሽያጭ የንብረት አጠባበቅና አጠቃቀም የፋይናንስና የሌሎች አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ጉዳዮች መመሪያ የማውጣት የመስጠትና የማስፈፀም መብት የፋብሪካው ነው፡፡ 

10.9. ለፋብሪካውና ለሠራተኛው ደህንነት እና እንዲሁም ለፋብሪካው ሀብትና ንብረት ጥበቃ ሲባል በመውጫና በመግቢያ በር ላይ ፍተሻ የማድረግ መብት አለው፡፡ 

10.10. በማንኛውም ስብሰባ ላይ የሌላውን ስብእና የሚነካ ወይም ባልተጨበጠ መረጃ ሀሰተኛ መልእክት ያስተላለፈ ወይም ሁከት እንዲፈጥር ያደረገ ሠራተኘን ፋብሪካው በህግ የመጠየቅ መብት አለው፡፡ 

አንቀጽ አስራ አንድ 

የአሰሪው ግዴታ 

11.1 በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚሁ ስምምነት ወይም በሌሎች የመንግስት ህጎች መመሪያዎችነና ደንቦች ላይ የተመለከቱትን መብቶችና ግዴታዎ በትክክል በሥራ ላይ ማዋል ግዴታ አለበት፡፡ 

11.2. ፋብሪካው በብሄረሰብ በጾታ በሀይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት በሠራተኞች መካከል ልዩነት አይደረግም፣ ሆኖም ግን ሴት ሰራተኞች ተሳትፎ ለማሳደግ በሚደረግ የእድገት የዝውውር የትምህርት እና ሌሎች ውድድሮች እኩል ነጥብ ሲመጣ ለሴቶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ መንግስት ለፆታ የሚሰጠውንም ሆነ የሰጠውን ድጋፍ እንደተጠበቀ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል የድጋፍ ነጥብ እንደተጠበቀ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል የድጋፍ ነጥብ ተጨምሮ የመጨረሻ ውጤት እኩል ከሆነ ለመለየት አግባብ ባለው መስፈርት እንዲበላለጡ ያደርጋል፡፡ 

11.3 ሊከፍል

የተስማማበት ደመወዝ እና ሌሎች ተከፋዮችን በተወሰነ ጊዜ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ 

11.4. ፋብሪካው ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ጥሬ ዕቃዎችንና መሣሪያዎችን ለሠራተኞች ማቅረብ እና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 12/1/ሀ እናለ መሰረት ግዴታ አለበት፡፡ 

11.6. ፋብሪካው ማንኛውንም የሰራተኛ ማህበር ወይም አባል በመሆኑና ባለመሆኑ ተጽእኖ ወይም አድልዎ አይደረግበትም፡፡ 

11.5. ሠራተኛ ሲቀጠር ሲመደብና የሥራ መደብ ለውጥ ሲያደርግ የሰራተኛው ፎቶ ግራፍ የተለጠፈበት የሚሠራበትን ቦታ እና የሥራ መደብ የሚያመለክት በተሸፈነ የመታወቂያ ካርድ በነፃ ፋብሪካው ይሰጣል፡፡ ካረጀ አሮጌውን አስረክቦ አዲስ ይለወጥለታል፤ ሆኖም ግን በአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከ5ዓመት በታች ላገለገለ መታወቂያ ካርድ ዋጋውን ብር 5.00/አምስት ብር/ ከፍሎ ይለወጥለታል፡፡ ከጠፋበት ግን በህጋዊ መንገድ ማረጋገጫ ሲያቀርብ ዋጋውን 5.00 /አምስት ብር/ ከፍሎ ይሰጠዋል፡፡ 

11.6. ሠራተኛ ሲቀጠር፣ ሲመደብና የሥራ መደብ ለውጥ ሲያደርግ የሰራተኛው ፎቶ ግራፍ የተለጠፈበት የሚሠራበትን ቦታ እና የሥራ መደብ የሚያመለክት በተሸፈነ የመታወቂያ ካርድ በነፃ ፋብሪካው ይሰጣል፡፡ ካረጀ አሮጌውን አስረክቦ አዲስ ይለወጥለታል፤ ሆኖም ግን በአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከ5ዓመት በታች ላገለገለ መታወቂያ ካርድ ዋጋውን ብር 5.00 /አምስት ብር/ ከፍሎ ይለወጥለታል፡፡ ከጠፋበት ግን በህጋዊ መንገድ ማረጋገጫ ሲያቀርብ ዋጋውን 5.00 /አምስት ብር/ ከፍሎ ይሰጠዋል፡፡ 

11.7የሰራተኛ ሲቀጠር፣ ሲመደብና የሥራ መደብ ለውጥ ሲያደርግ የሰራተኛው ፎቶ ግራፍ የተለጠፈበት የሚሠራበትን ቦታ እና የሥራ መደብ የሚያመለክት በተሸፈነ የመታወቂያ ካርድ በነፃ ፋብሪካው ይሰጣል፡፡ ካረጀ አሮጌውን አስረክቦ አዲስ ይለወጥለታል፣ ሆኖም ግን በአያያዝ ጉድለት ምክንያት ከ5ዓመት በታች ላገለገለ መታወቂያ ካርድ ዋጋውን ብር 5.00 /አምስት ብር/ ከፍሎ ይለወጥለታል፡፡ 

11.8. ፋብሪካው የሰራተኛው ጥቅም የተሳሰረ መሆኑን በመረዳት ምርት መገልገያዎችና ማንኛውም የፋብሪካው ሀብትና ንብረት በጥንቃቄ እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ 

11.9. ማንኛውም ሰራተኛ ቅጥር፣ እድገት፣ ቅጣት እና ስንብት ውሳኔ በሚመለከት ለሰራተኛ ማህበሩ ያሳውቃል፡፡ 

11.10. አዲስ የሚቀጠሩ ሠራተኞችን ፋብሪካው እንደ አስፈላጊነቱ በራሱ ወጪ ጤንነታቸውን ያመረምራል፡፡ 

11.11. ሠራተኛው የተቀጠረበትን ቀን የደመወዝ ልክ የትምህርት ማስረጃ የሥራ ልምድ የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም /ግምገማ/ እድገት ያገኘባቸውን ማስረጃዎች ስልጠናዎች እና ትምህርት የወሰደባቸው ፈቃዶች ጤንነት ሁኔታዎች የመሳሰሉትን በግልጽ በሚያሳይ መዝገብ በጥንቃቄ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡ 

11.12. በዚሁ ህብረት ስምምነት የዲሲፕሊን እርምጃዎች አወሳደድ የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓትና የመሳሰሉትን ጉዳዮች አፈፃፀም መከታተል ግዴታ አለት፡፡ 

11.13. ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ያመቻቻል አደጋ መከላከል የሚያገለግሉ እና አደጋ በደረሰበት ጊዜ ለመጀመሪያ እርዳታ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን የመጸዳጃና የሰውነት መታጠቢያ ክፍሎችን ከነፅዳት ሰራተኞቻቸው አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 

11.14. ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በተመደበበት ሥራ የሥራ ዝርዝር መግለጫ /ጆብ ዲስክሪብሽን/ በተጨማሪም ሠራተኛው የሚጠበቅበትን የሥራ ውጤት /የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም መለኪያ ግብ/ አውቆ በሥራ ላይ እንዲውል አዘጋጅቶ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ 

11.5. የሥራ ውል በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛው በሚጠየቅበት ጊዜ ሰራተኛው ሲሰራ የነበረውን የሥራ ዓይነት የአገልግሎት ዘመኑና ሲከፍለው የነበረው ደመወዝ እሚያሳይ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡ 

11.6. ይህን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም በአዳዲስ የስራ ሁኔታዎች ላይ ሠራተኛ ማህበሩ ሲጠይቅ ቀርቦ የመወያየት ግዴታ አለበት፡፡  

አንቀጽ አስራ ሁለ

ፋብሪካው ለሰራተኛ ማህበሩ የሚሰጠው ግልጋሎት 

  1. የሠራተኛ ማህበሩን ሥራ ለማከናወን እንዲረዳ ወንበር ከጠረጴዛ ጋር ይሰጣል፡፡ 

የሠራተኛ ማህበሩ ማስታወቂያ ትምህርታዊ ጽሁፍ የሚለጠፍበት የማስታወቂያ ሰሌዳ በተቻለ መጠን ያዘጋጃል፡፡ 



አንቀጽ አሥራ ሶስት  

የሠራተኛ ማህበሩ መብት 

13.1. በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ ስለተመለከቱትም ሆነ ከስምምነቱ ውጪ ሊያጋጥም ስለሚችል ማናቸውም የሠራተኛው የሥራ ሁኔታዎች ሠራተኛውንም ወክሎ ከአሰሪው ጋር የመነጋገር መብት አለው፡፡ 

13.2. ቅሬት ወይም በደል ደረሰብን የሚሉ ሰራተኞች ወክሎ ከአሰሪው ሠራተኛው ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96፣494/98 እና የህብረት ስምምነት በሚፈቅደው መሠረት በመደራደር ወይም ሠራተኛን/ ሠራተኞችን ለመከራከር መብት አለው፡፡ 

13.3. በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 82 እና በህብረት ስምምነት በተወሰነው መሰረት የማህበሩ መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ የህብረት ስምምነት ለመደራደር ለማህበሩ ስብሰባ ለመገኘት በሴሚናሮችና በስልጠና ለመካፈል እንዲችሉ ከአንድ የሥራ ቀን 24ሰዓት/ በፊት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ የመጠየቅ መብት አለው፡፡   

13.4. ሠራተኛ ማህበሩ ስለ ሠራተኛ ሁኔታ ከሌላ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ ማብራሪያ የመስጠትና የመነጋገር መብት አለው፡፡ 

13.5. ፋብሪካው በሚዘረጋው አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች እና ማሻሻያዎች ላይ ሠራተኛ ማህበሩ የማወቅ መብት አለው፡፡ 

አንቀጽ አሥራ አራት 

የሰራተኛ ማህበሩ ግዴታዎች 

14.1. የህብረት ስምምነቱ የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅን ትርጉምና አፈፃፀም ከፋብሪካው ጋር በመተባበር ሠራተኛው እንዲረዳ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ 

14.2. ይህንን የህብረት ስምምነት ለማሻሻል ወይም በአዳዲስ የሥራ ሁኔታዎች/ የአሰራር ስርዓቶች እና ማሻሻያዎች/ ላይ ፋብሪካው ለውይይት ሲጠራ ቀርቦ የመወያየት ግዴታ አለበት፡፡

14.3. የህብረት ስምምነቱን ህጎችና መንግስታዊ መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ አሰሪው የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና ደንቦች የሥራ ዕቅዶችን ለማስፈፀም የመተባበር እና የመፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ 

14.4. በፋብሪካው የሥራ አካባቢዎች ሠራተኛው ዲሲፕሊን እንዲያዳብርና ኢንዱስትሪ ሰላምም አንዲሰፍን ግዴታ አለበት፡፡ 

14.5. ሠራተኛው የሥራ ሰዓት አክብሮ መላ ጉልበቱንና ችሎታውን በሥራ ላይ አውሎ ምርቱን በጥራትና በብዛት እንዲያመርትና የፋብሪካው እቅድ ግቡን እንዲመታ የማስተማር ግዴታ አለበት፡፡ 

አንቀጽ አሥራ አምስት

የሰራተኛ መብት

15.1. ሴት ሠራተኞች ሲመጡና ሲገቡ የሚፈተሹት በሴት ሰራተኛ ነው፡፡ 

15.2. በህግ ወይም በዚህ የህብረት ስምምነት በሠራተኛ ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሥራ ደንብ በተወሰነው ወይም በፍ/ቤት ተዕዛዝ መሠረት ካልሆነ ወይም ሠራተኛው በጹሁፍ ካልተስማማ በስተቀር ፋብሪካው ከሠራተኛው ደመወዝ ሲቀነስ ወይም በዕዳ ሊይዝ ወይም ሊያቻችል አይችልም፡፡ 

15.3. በመንግስት ህጎች መመሪያዎች በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ በተጠቀሱት የሥራ ሁኔታዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው፡፡ 

15.4. የሚገባውን ደመወዝና ሌላም ህጋዊ ወይም ጥቅም በወቅቱ የማግኘጥ መብት አለው፡፡ 

15.5. ማንኛውም የፋብሪካው ሠራተኛ ማህበሩ አማካኝነት ወይም በግሉ ቅሬታውን ወይም አቤቱታውን ለሥራ ክርክር ችሎታ ሕጋዊ መብቱን ለማስከበር ይችላል፡፡ 

15.6. ማንኛውም ሠራተኛ በግል ማህደሩ ላይ ጥርጣሬ ሲኖረው በአንድ ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ በሰው ሀብት ልማት አመራር ክፍል እና በሠራተኛው ማህበሩ በኩል አስቀርቦ ለማየት መብት አለው፡፡ 

15.7. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 እንደተጠበቀ ሆኖ በሠራተኛ ጥፋት ወይም ቸልተኝነት ሳይሆን በመሣሪያ ብልሽት ወይም በጥሬ እቃ እጥረት ሠራተኛ ሳይሰራ ቢውል የዕለቱን መደበኛ ደመወዝ የማግኘት መብት አለው፡፡ 

15.8. ሠራተኛው በማንኛውም ስብሰባ ወይም በማንኛውም ህጋዊ መንገድ ሃሳቡንና ቅሬታውን የመግለፅና የማቅረብ መብት አለው፡፡ 

15.9. ማንኛውም የፋብሪካው ሠራተኛ የሆነ ወይም የነበረ አስፈላጊውን የበር መግቢያና መውጫ ፎርማሊቲ አሟልቶ የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ወደሚመለከተው ክፍል የመቅረብ መብት አለው፡፡ 

15.10. ማንኛውም ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሙ የተገኘበት ሰራተኛ ስለተገኘበት ብቻ ከመደበኛ ሥራው ላይ ምንም ዓይነት አድሎና መገለል አይደረግበትም፡፡ 

15.11. የዕድሜ ጣርያው ለጡረታ የደረሰ ሠራተኛ ጡረታ ከሚወጣበት ጊዜ 12 ወራት ቀድሞ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡ የጡረታ ጊዜው ደርሶ የጡረታ ደብተሩ ያልደረሰውና ቀሪ ሥራ የሚቀረው ከሆነ እስከ 6 ወራት ለሚደርስ ጊዜ ፋብሪካው በኮንትራንት ቀጥሮ እያሰራው እንዲቆይ ያደርጋል፡፡ 

15.12. ደመወዝ እና ሌሎ ክፍያዎችን በወቅቱ ተገኝት ለመቀበል ካልቻለ ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚውል የሰው ሀይል ልማትና አመራር ክፍል በሚዘጋጀው ቅጽ ላይ ማረጋገጫ በመስጠት ለወኪሉ እንዲከፈልለት ያደርጋል፡፡ 

አንቀጽ አሥራ ስድስት 

የሠራተኛ ግዴታዎች 

16.1. በቅልጥፍና በተሟላ ትጋት ሥራውን የማከናወን ግዴታ አለበት፡፡ 

16.2. በአሠሪውና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በዚህ ህብረት ስምምነትና ለሥራ ማሻሻያ ከመንግስትና ከፋብሪካው የሚተላለፉትን ደንቦችና መመሪያዎች የማክበር ግዴታ አለበት፡፡

16.3. ማንኛውም የፋብሪካው ሠራተኛ አስቀድሞ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር በመደበኛ ሥራው ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡ 

16.4. በፋብሪካው ላይ በፋብሪካ ላይ ወይም በሥራ ባልደረቦች በሚያጋጥም ጉዳት ወይም አደጋ ላይ በተፈለገው ሁኔታ ሁሉ እርዳታ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ 

16.5. ለሥራው አስፈላጊ ሆነው የተሰጡትን መሣሪያዎች እና ሌሎች ንብረቶችን በጥንቃቄ መያዝና የሥራው ሰዓት ሲፈፀም በሚገባ የማስቀመጥ ግዴታ አለበት፡፡ 

16.6. ለሥራው ወይም ለፋብሪካው ጥሩ ስም በሚያስገኝ መንገድ ሁልጊዜ እራስን እና አካባቢን የመንከባከብ የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡ 

16.7. የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም ሥርዓት የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡ 

16.8. በፋብሪካው ወይም በፋብሪካው መሣሪያዎች ላይ የሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት የሚጎዳ ጉድለትና ሲያገኝና የሚደርሰውን ማንኛውም አደጋ ወድያውኑ ለአሰሪው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ 

16.9. በሥረቃ ላይ መተባበር ለፋብሪካው ጥቅም የለውም እንቅስቃሴ አሰራር ላይ አንድነት የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡ 

16.10. ማንኛውም ሠራተኛ ከሚመለከተው ኃላፊ የፅሁፍ ፈቃድ ሳይቀበል የፋብሪካው ንብረት የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምርት ወይም ጥሬ እቃ መገልገያ ዕቃ /ቱልስ/ ከፋብሪካው ቅጥር ግቢ በማውጣት ለራሱ /በግል/ ሲገለገልበት ወይም ለሌላ ግለሰብ አሳልፎ ለመስጠትና ከጥቅም ውጭ ማድረግ የለበትም፡፡ 

16.11. በአሰሪውና በሠራተኛው ማህበር ወይም በአሠሪውና በሠራተኛ መካከል ወይም በሠራተኛ መካከል ያለመግባባት የመፍጠር የሀሰት ወሬ አሉባልታ መንዛትና ጠብ ማንሳት ወይም እንዲነሳ መገፋፋት ወይም እራሱን ሆነ ጓደኞቹን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም የፋብሪካው ጥቅም የሚነካ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወድያውኑ ለአሰሪው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ 

16.12. ማንኛውም ሠራተኛ በፋብሪካ የሥራ ሰዓት በፋብሪካው ግቢና በማምረቻ ቦታዎች ላያስገባ የሚችል ችግር ሲያጋጥመው በቅድሚያ መታወቂያውን በማስያዝ የት ክፍል እንደሚሄድ ለጥበቃ ክፍል በማሳወቅ መግባት ይኖርበታል፡፡ 

16.13. ማንኛውም ሠራተኛ በመደበኛ የስራ ሰዓት እንቅልፍ መተኛት የለበትም፡፡ 

አንቀጽ አስራ ሰባት

የሥራ ውል አመሠራረት የሠራተኛ ቅጥር ምደባ ሥልጠና፣ ግምገማ፣ ዕድገትና ዝውውር

17.1. ጠቅላላ 

17.1.1. ፋብሪካው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ሕግን ተከትሎ በሚወጣ የፋብሪካው መመሪያና በዚህ ሕብረት ስምምነት መሰረት ሠራተኛን መቅጠር፣ ማሳደግ፣ ለሥራ ብቃት ያለው ነው ብሎ ያመነበትን ሠራተኛ አወዳድሮ ለመመደብ ወይም አዛውሮ ለማሰራት ይችላል፡፡ 

17.1.2. በአዋጅና ሌሎች መመሪያዎች የተሰጡትን ግዴታዎችንና ህግን ተከትሎ ፋብሪካ የሚወጣቸውን መመዘኛ የሚያሟላና ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከተገኘ በሃይማኖት፣ በጾታ፣ በብሔርና በፖለቲካ ልዩነት ሳይደረግበት በፋብሪካው በሚፈጠሩ ክፍት ቦታዎች ይወዳደራል፡፡ 

17.1.3. በፋብሪካው መስፋፋት ወይም የምርት እድገት የተለየ ሙያን የሚጠይቅ ተጨማሪ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን አዲስ የሥራ ቦታ መፈጠሩን ወይም በተለያየ የሥራ ቦታዎች ሠራተኛ መመደብ አስፈላጊ መሆኑን ህግን ወይም ህብረት ስምምነትን ተከትሎ የሚወሰነው አሰሪው ነው፤ ፋብሪካው እንደ ስራው ፀባይና እንደስራው ብዛት ወይም አመቺነት ሠራተኛን ላልተወሰነ ጊዜ ወይም በተወሰነ ጊዜ ሊቀጠር ይችላል፡፡ 

17.1.4. በተለቀቀም ሆ አዲስ በተፈጠረ የሥራ መደብ የሚፈለገውን የትምህርት ደረጃና የሙያ አይነት፣ እንዲሁም ተፈላጊውን የሥራ ልምድ የሚወስነው ፋብሪካው ነው፡፡ 

17.1.5. ለሥራ ብቁ መሆን ለታመነበት ሠራተኛ የቅጥር ደብዳቤው ከመስጠቱ በፊት ተቀጣሪው ሠራተኛ ፋብሪካው የሚጠይቃቸውን መረጃዎች በቅድሚያ የሟሟላት ግዴታ አለበት፡፡ 

17.1.6. ፋብሪካው መንግስት ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ ሠራተኛ ሲቀጠር ዋስ እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡ 

17.1.7. አዲስ ወይም ነባር ሠራተኛ ፋብሪካው በሚያወጣው ዕቅድ መሠረት ማንኛውም የሙያ ደህንነትና ጤንነት ስልጠና በፋብሪካው በነፃ ይሰጠዋል፡፡ 

17.2. የሠራተኛ አቀጣጠር ሥርዓት 

ሠራተኛ ሊቀጠር የሚችለው ከዚህ በታች በተመለከቱት ምክንያት ነው፤ 

17.2.1. ለፋብሪካው መስፋፋት ወይም የምርት ዕድገት የተለየ ሙያ የሚጠይቅ ተጨማሪ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን ፋብሪካው ሲወስን፣ 

17.2.2. አዲስ የሥራ መደብ ተፈጥሮ ወይም ነባር የሥራ ቦታ ተለቆ ወይም ተቀይሮ /ተዳልኮ/ በፋብሪካው ማኒንግ ቴብል መሠረት ለቦታው የወጣውን መስፈርት የሚያሟላ ሠራተኛ ከፋብሪካው ሠራተኞች ውስጥ ሲታጣ፤ 

17.2.3. ለተወሰነ ሥራ ወይም ለተወሰነ ጊዜ መመሪያን በመከተል ሠራተኛ የሚቀርበት ሁኔታ ሲያጋጥም፤ 

17.2.4. በህጉ መሠረት የውጭ አገር ጊዜ መቅጠር ሲያስፈልግ፤ 

17.3. የሥራ ውል አመሠራረት፤ 

17.3.1. ማንኛውም የሥራ ውል የስራውን ዓይነት፣ ቦታ፣ ለስራው የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን የስሌትን ዘዴን፣ የአከፋፈሉን ሁኔታና ጊዜ የሙከራ ጊዜ እና የተቀናጀ የስራ አፈፃፀም መለኪያ ግብር ውሉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መያዝ ይኖርበታል፡፡  

17.3.2. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ መንግስት በየጊዜው የሚያወጣቸው መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ህብረት ስምምነት ከስራ ውል እንደ አንዱ ክፍል የሚቆጠሩ ይሆናል፡፡ 

17.3.3. ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ሠራተኛ የሚቀጠረው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 10 መሠረት ነው፡፡ 

17.4. የሙከራ ጊዜ፣ 

17.4.1. የማንኛውም የቋሚ ስራ ተቀጣሪ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜ ከ45 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም፣ ይህም ለሠራተኛው በጽሁፍ ይገልፃል፡፡ 

17.4.2. የሙከራ ጊዜ ላይ ያለ ሠራተኛ ለስራው ብቁ ካልሆነ ፋብሪካው ያለምንም ማስጠንቀቂያ የስራ ስንብት ክፍያ የአገልግሎት ክፍያና ካሣ ሳይከፍል ሊያሰናብት ይችላል፡፡ 

17.4.3. ሠራተኛው በሙከራ ጊዜው መጨረሻ በአሠሪው አስተያየት ስራው አጥጋቢ ከሆነ በውሉ መሠረት የተቀጠረ ለመሆኑ በጽሑፍ ይረጋገጣል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው የሙከራ ጊዜው ካለቀ በኋላ ስራውን ከቀጠለ በውሉ መሠረት ለታቀደው ጊዜ ወይም ስራ እንደተቆጠሩ ይቆጠራል፡፡ 

17.4.4. በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ እንደ ስራው ፀባይ የአደጋ መከላከያ ይሰጠዋል፤ ሆኖም የሙከራ ጊዜውን ከመጨረሱ በፊጽ ለቋሚ ሠራተኛ የሚሰጠውን ጥቅማ ጥቅም ሊያገኝ አይችልም፡፡ 

17.4.5. ቀድሞ የፋብሪካው ሠራተኛ የነበረ ሲሠራበት ከነበረው የስራ መደብ ተመሳሳይና ተመጣጣኝ ቦታ ላይ ወይም ደግሞ ፋብሪካው የሠራተኛውን የቀድሞ ብቃትና በሌላ መስሪያ ቤት ሲሠራባቸው የነበሩ የስራ መደቦች በቂ መሆናቸውን ሊያምንበት ተመጣጣኝ የሥራ መደብ ባይሆንም እንደገና ከተቀጠረ የሙከራ ጊዜ አይኖረውም፡፡ 

17.5. ሥልጠና፤ 

17.5.1. አሠሪው ሠራተኛው እውቀቱን አሻሽሎ የተመደበበትን ሥራ ብቃት እንዲወጣ ከቅጥር በፊት ስራውን ከሠራተኛ ገር ለማስተዋወቅ የሙከራ ጊዜያቸውን የጨረሱ ሠራተኞች ያላቸውን እውቀት አሻሽለው የተመደቡበትን ስራ በብቃት እንዲወጡ ወይም በእድገትና በዝውውር ምክንያት በተጨማሪ ኃላፊነትና የሥራ ብቃት ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊነቱን አሰሪው ካመነበት ፋብሪከው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አቅም በፈቀደ መጠን ስልጠና በነፃ ይሰጣል፡፡ 

17.5.2. በአሰሪው ታምኖበት በማሰልጠኛ ኮርስ የተካፈሉ ሠራተኞች ኮርሱን ከፈፀሙ በኋላ የተከታተሉትን የትምህርት ዓይነት ያገኙትን እውቀትና የሰለጡትን ሙያ የሚያስረዳ ከአሰልጣኝ ድርጅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት ወይም በድርጅቱ ለመሰልጠናቸው የሥልጠና ክፍሉ የሚሰጣቸውን መረጃ ለሰው ኃይል ልማት አመራር ክፍል አቅርበው በማህደራቸው እዲያዝ ያደርጋል፡፡ 

17.5.3. በማንኛውም ሁኔታ በስልጠና ላይ የቆየ ሠራተኛ የስልጠና ሪፖርት እንዲሁም የሰለጠነበትን ማኗል ኮፒዎች ሰው ኃይል ልማትና አሠራር ክፍል መስጠትና የሰለጠነውን ስልጠና ለሌሎ እንዲያሰለጥን ሲጠየቅ ተዘጋጅቶ ስልጠና ይሰጣል፡፡ 

17.5.4. ፋብሪካው ሠራተኞች እውቀታቸውን በትምህርት እንዲያሻሽሉ ያነቃቃል፤ ሆኖም የሠራተኛው ማኗል ኮፒዎች ሰው ኃይል ልማትና አሠራር ክፍል መስጠትና የሰለጠነውን ስልጠና ለሌሎች እንዲያሰለጥን ሲጠየቅ ተዘጋጅቶ ስልጠና ይሰጣል፡፡ 

17.5.5. ከ1ኛ-10 ክፍል ሠራተኛው እንዲማር ትምህርት ቤቱን ስም በቅድሚያ ጠቅሶ ሲጠይቅና በአሰሪው በጽሑፍ ሲፈቅድ ብቻ ትምህርት መማር ይችላል፡፡ የክፍያውም ሁኔታ በመንግስት የትም/ተቋም ከሆነ 50% በግል የትምህርት ተቋም ከሆነ ድርጅቱ በመንግስት ት/ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ከሚከፈለው ያልበለጠ ወጭ ይሸፍናል፡፡ ሠራተኛው በድርጅቱ ወጭ ትምህርቱን ከተከታተለ በወሰድው ጊዜ መጠን ለፋብሪካው አገልግሎት መስጠት አለበት፤ በትምህርት ባሳለፈው ጊዜ መጠን አገልግሎት ሳይሰጥ የሥራ ውሉን ካቋረጠ ፋብሪካው የከፈለውን የትምህርት ወጭ የባንክ ወለድ ታክሎበት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ 

17.6. የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም ምዘና፤ 

17.6.1. የተቀናጀ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሠራተኛው ያለው አዕምሮአዊና አካላዊ ችሎታውን በመጠቀም በፋብሪካው ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ የተቀመጡትን ተግባራት ማከናወኑን በተቀናጀ ሁኔታ ለመመዘን የሚረዳ የምዘና ሥርዓት ነው፡፡ 

17.6.2. የተቀናጀ የስራ አፈፃፀም ምዘና ሪፖርት በፋብሪካው መመሪያ መሠረት ይሞላል፡፡ 

17.6.3. የተቀናጀ የስራ አፈፃፀም ምዘና ሪፖርት በሠራተኛው የቅርብ የሥራ ኃላፊ በአንድ ቅጅ ተሞልቶ በየደረጃው ባሉት የሥራ ኃላፊዎች በፀደቀ በኋላ ለሰው ኃይል ልማትና አመራር ክፍል ይላካል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ስምንት

ተተኪ ሠራተኛ ስለመመደብ 

18.1. ተተኪ ሠራተኛ የሚመደበው አንድ የሥራ መደብ ክፍት ሲሆንና ቋሚ ሠራተኛ እስኪመደብ ወይም አነድ ሠራተኛ ለተወሰነ ጊዜ በስራ ጉዳይ በህመም በዓመት እረፍትና በመሳሰሉት ምክንያት ከስራ ገበታው ሲለይ ጊዜያዊ ሠራተኛ በቦታው መመደብ በማይቻልበት ወይም አስፈላጊ በማይሆንበት ጊዜ የስራ መደቡን ለመሸፈን ነው፡፡

18.2. በተተኪነት የሚመደበው ሠራተኛ ለክፍት ቦታው አሰሪው ይመጥናል ብሎ ያመነበት ይሆናል፤ እንዲህ አይነቱ ሠራተኛ የማይገኝ ከሆነ ወይም ተተኪ ሠራተኛ መመደብ አስፈላጊ ካልሆነ የስራ መደቡ የሚገኝበት ኃላፊ ስራውን ደርቦ እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ 

18.3. ተተኪ ሠራተኛ የሚመደበው የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ በቅድሚያ በማስፈቀድ ሲሆን ለተተኪው በደብዳቤ ይገለጽለታል፡፡ 

18.4. በተተኪነት ለተመደበ ሠራተኛ የተኪነት አበል ክፍያ የደመወዙን 25% ይሆናል፤ ይሁንና የተተኪነት አበል ክፍያ ከሠራተኛው ደመወዝ 250 ብር መብለጥ የለበትም፤ እንዲሁም የተኪነት አበል የሚታሰበው ከሱፐርቫይዘር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የሥራ መደቦች ይሆናል፡፡ ከዚያ በታች ለሆኑ የሥራ መደቦች በተተኪነት ለሥራ ሠራተኛ በጽሁፍ የሥራ ልምዱ እንዲያዝለት ይደረጋል፡፡ 

18.5. ተተኪ ሠራተኛ አበል የሚከፈለው የራሱን ሥራ እየሰራ የሚተካበትን ስራ ደርቦ የሚሰራ ሠራተኛ እና ከዚያው የስራ መደብ በላይ ሲሆን ነው፤ የበታች ሠራተኛን ስራ ደርቦ የሚሰራ ሠራተኛ የተተኪነት አበል አይከፈለውም፡፡      

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ 

ስንብት፣ 

19.1. የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አዋጅ ቁጥር 494/98 መንግስት ወደፊት የሚያወጣቸው አዋጆች እና ህብረት ስምምነት መሠረት ይሆናል፡፡ 

19.2. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና ከዚህ ህብረት ስምምነት መሠረት ከስራው የሚሰናበት ማንኛውም ሠራተኛ ተገቢ መብቱን ሁሉ ለማግኘት ይችል ዘንድ በቅድሚያ በእጁ ያሉትን የፋብሪካውን ንብረቶች በሙሉ ለፋብሪካ ማስረከቡ መረጋገጥ አለበት፡፡ 

19.3. የሥራ ውሉ ተቋርጦ ለሚሰናበት ሠራተኛ በአንቀጽ 15.2 የተጠቀሰውን በቅድሚያ ካሟላ በኋላ ተገቢው ክፍያና የምስክር ወረቀት ከሰባት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡ 

19.4. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟላ የምስክር ወረቀት ሠራተኛው ሲጠይቅ በአማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ወይም በሁለቱም ቋንቋዎች ይሰጠዋል፡፡ 

ሀ/ የሠራተኛው ስም 

ለ/ የሥራው ዓይነት 

ሐ/ የሥራ መደብ 

መ/ የአገልግሎት ዘመን 

ሠ/ ሠራተኛው በሥ ላይ እያለ የነበረው እንቅስቃሴ መግለጫ 

ረ/ ይከፈለው የነበረውን ደመወዝ 

19.5. የማንኛውም ሠራተኛ የስንብት ክፍያ የሚፈፀመው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ወይም 494/98 መሠረት ነው፡፡ 

19.6. አዋጅ ቁጥር 377/96 እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሠራተኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከስራው ቢለይና ወደ ስራው ለመመለስ ቢያመለክት በምትኩ ስራ ቦታው ላይ ሌላ ሠራተኛ ያልተመደበበት ከሆነና ሠራተኛው ለስራው አስፈላጊ መሆኑን ሲያረጋግጥ ፋብሪካው ወደ ስራው ሊመልሰው ይችላል፡፡ 

አንቀጽ ሃያ

20.1. የሥራ ሰዓት፣ የህዝብ በዓላት፣ የትርፍ ሰዓትና የሣምንት የዕረፍት ቀን፡ 

20.1.1. መደበኛ የሥራ ሰዓት በቀን ከ8 ሰዓት ወይም በሳምንት ከ48 ሰዓት አይበልጥም፤ 

20.1.2. የስራ ሰዓት አቆጣጠር ከዚህ በታች እንደተመለከተው ነው፡፡ 

20.1.2.1. ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 

ለጧት ገቢ ከጧቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት 

ቀን ገቢ ከቀኑ 9፡00ሰዓት እስከ ምሸቱ 5፡00 ሰዓት 

ለሊት ገቢ ከምሽቱ 5፡00ሰዓት እስከ ጧት 1፡00ሰዓት 

ለአዳር ፈረቃ ሠራተኞች 30 ደቂቃ ለእራት ጊዜ ይኖረዋል፡፡ 

20.1.2.2. በመደበኛ ሰዓት/ከፈረቃ ውጭ ለሚገቡ 

20.1.2.2.2.1 ከሰኞ እስከ አርብ ጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ6፡00ሰዓት 

ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 1፡00ሰዓት 

20.1.2.2.2. ቅዳሜ 

ከጧቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00ሰዓት  

20.1.3. በማንኛውም የሥራ ወይም በሳምንት እረፍት ቀን ወይም በህዝብ በዓላት ቀን በአሰሪው መስራት አለበት ተብሎ በታመነበት የስራ ቦታ የሚሠሩ ሠራተኞች እንደአስፈላጊነቱ በስራ ላይ አንዲገኙ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 

20.2. የሕዝብ በዓላት

20.2.1. ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሕዝብ በዓላት ቀን ይሆናል፡፡ ሆኖም አግባብ ባለው የመንግስት ህግ የሚሻሻል ከሆነ በህግ የተሻሻለው ተግባራዊ ይሆናል፡፡  

  1. መስከረም 1 ቀን ዘመን መለወጫ 
  2. መስከረም 17 ቀን መስቀል 
  3. ታኅሣሥ 29 ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 
  4. ጥር 11 ቀን ጥምቀት 
  5. የካቲት 23 ቀን የአድዋ ድል መታሰቢያ 
  6. ሚያዝያ 27 ቀን ድል በዓል 
  7. ሚያዝያ 23 ቀን ዓለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን /ሜይዴይ/
  8. ኢድ አልፈጥር /ረመዳን/ 
  9. ስቅለት 
  10. ትንሳኤ 
  11. ኢድ አልአድሀ /አረፋ/
  12. መውሊድ  /የነብዩ መሀመድ ልደት/
  13. ግንቦት 20 እና መንግስት ወደፊት የሚያወጣቸው በዓላት 

    20.3. የትርፍ ሰዓት ሥራ 

    20.3.1. ስለትርፍ ሰዓት ሥራ የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎችን ስለአከፋፈሉም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአንቀጽ 66 68 በተዘረዘረው መሠረት ይፈፀማል፡፡  


    የሥራ ውል በመቋረጥ ምክንያት የሚደረግ ክፍያና ካሳ

    21.5.1. የሥራ ውሉ በማረጡ ምክንያት የሚከፈል የስንብት ክፍያ ካሳ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና አዋጅ ቁጥር 494/98 መሠረት ይፈጸማል፡፡ 

    አንቀጽ ሃያ ሁለት 

    አመታዊ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ

    22.1. ፋብሪካው ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪ እና ቦነስ የሚሰጠው የፋብሪካው ሠራተኞች ለሥራ ለማነቃቃትና ፋብሪካውን ትርፋማ ለማድረግ ታስቦ ሲሆን የቦነስ እና አመታዊ ጭማሪ አሰጣጡም የፋብሪካው አመታዊ የትርፍ መጠን ከታክስ በኃላ የተጣራ ትርፍ ብር 3000000.00 (ሶስት ሚሊዬን ብር) እና ከዚያ በላይ ሲገኝ በፋብሪካው ውስጥ በበጀት ዓመቱ ከ6 ወራት በላይ አገልግሎት ለሰጠ የአንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይደረግለታል፡፡ 

    እንዲሁም ቦነስ የአንድ ወር ደመወዝ ይሰጣል ሆኖም በበጀት ዓመቱ ሙሉ አስራ ሁለት ወራት ያልሰራ ከሆነ በሰራበት ወራት መጠን ታስቦ ይከፈለዋል፡፡  

    ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እንዳሉ ሆኖ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪና ማግኘት የሚችሉት በበጀት ዓመቱ አማካይ የሥራ አፈጻጸም ውጤታቸው ቢያንስ 70% እና ከዚያ በላይ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ 

    የድርጅቱ አመታዊ የኦዲት ሪፖርቱን የማህበሩ ኮሚቴዎች ከሚመለከተው ኃላፊ ዘንድ በመቅረብ ሊያዩት ይችላሉ፡፡ 

    አንቀጽ ሃያ ሶስት

    የደመወዝ ክፍያ ሥርዓት እና የበጀት አመት 

    23.1. ኩባንያው የሚቀጥረው ወይም የሚመድበውን ሠራተኛ በደመወዝ ስኬል መሠረት ይከፍለዋል፡፡ 

    23.2. ኩባንያው ላሉት የሥራ መደቦች የደመወዝ እስኬል ሥርዓት ይኖረዋል፡፡ 

    23.3. የኩባንያው የበጀት ዓመት እ.ኤ.አ ሐምሌ 1 ቀን ተጀምሮ ሰኔ 30 ይጠናቀቃል፡፡ 

    አንቀጽ ሃያ አራት 

    የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ

    የሕክምና አገልግሎት ላይ ፋብሪካው መንግስት በሚያወጣው የጤና መድን ሽፋን የሚጠቃለል ሆኖ ይህ ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ አሰሪው ከስር የተዘረዘሩትን ነገሮች ይሟላል፡፡  

    1. የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ የሚሰጡ በየፈረቃው 2 ሠራተኞች ያስለጥናል፡፡ 
    2. ለመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ፋብሪካው ያሟላል፡፤ 
    3. ቀደም ሲል በፋብሪካው በልምድ ሲሰራባቸው የነበሩ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ እንደነበር ቀጥሏል፡፡ 
    4. የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማወቅ ሠራተኞች እንዲመረመሩ ያበረታታል፡፡ አስፈላጊ የሆኑ እገዛዎችንም ያደርጋል፡፡ 
    5. በሕጋዊ መንገድ ተመርምረው የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው መኖር ተረጋግጦ መደሃኒት ሲታዘዝላቸው ፋብሪካው ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር መድሃኒት የሚያገኙበት መንገድ ያመቻቻል፡፡ 
    6. በሕጋዊ መንገድ ተመርምረው በደማቸው ኤች አይ ቪ ቫይረስ ለተገኘባቸው ሠራተኞች የሕክምና ፈቃድ ይሰጣል እንደማንኛውም ሕመም ሳይታይ ልዩ እገዛም ይደረግላቸዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ 377/96 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆን ነው ሌላው በቀረበው ጥራዝ ላይ ያለው በሙሉ የድርጅቱን አቅም ያገናዘበ ባለመሆኑ ሁለቱም ወገኖ እንዲወጣ ተስማምተዋል፡፡  
    1.  

    አንቀጽ ሃያ ሰባት 

    ኢንሹራንስ 

    27.1. አንድ ሠራተኛ ሥራ ተግባሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቤቱ ሲመለስ 1.00ሰዓት ወይም የሥራ ተግባራን ለመፈጸም ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት 1፡00ሰዓት በስራ ጉዳይ ከቤታቸው ተጠርተው የሚመጡትን ሠራተኞች ያጠቃልላል፡፡ በማንኛውም ወቅት ፋብሪካው ሠራተኞች ለድርጅቱ ሥራ ሲንቀሳቀሱ ለሚደርስባቸው ጉዳት በኢንሹራንስ ይሸፈናል፡፡ 

    27.2. በዚህ አንቀጽ መሠረት የኢንሹራንስ መብት ያለው ሠራተኛ ሁሉ ለደረሰበት ጉዳት በ24ሰዓት ውስጥ ወይም ፋብሪካው ለሰው ኃብት ልማት አመራር ማስመዝገብን በቂ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ ጉዳት የደረሠበት ሠራተኛ ሪፖርት ለማድረግ የአደጋውን ሁኔታ ያየ ማንኛውም ሰው በተወሰነው ሰዓት ውስጥ በምስከርትን መዝግቦ ማመልከት አለባቸው፡፡ በተወሰነው ጊዜ ያልተመዘገበ ጉዳት ተቀባይነት የለውም ለፋብሪካው ሪፖርት ማድረግ ካልተቻለ ከፖሊስ ጣቢያ ወይም ከአካባቢው ቀበሌ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡ 

    27.3. በሥራ ላይ ሳለ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳቱን ሁኔታ የክፍሉ ኃላፊና 3/ሶስት/ ምስክሮች ፈርመውበት ለፋብሪካው ሰው ኃብት ልማት አመራር ያስረክባል፡፡ ይኸውም በካርድ ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ 

    27.4. አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ በኢንሹራንስ ክሌይም ምክንያት ሳይጉላላ በአፋጣኝ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ የኢንሹራንስ ክሌይም በፋብሪካው የሰው ኃብት ልማት አመራር አማካይነት ይላክለታል፡፡ 

    27.5. በሥራ ላይ አደጋ የደረሰበት ሠራተኛ የካሳ ክፍያ 

    27.6. ከገቢ ግብር ነፃ ነው፡፡ 

    27.7. ሊተላለፍ ሊከበር ወይም በዕዳ ማቻቻይነት ሊያዝ አይችልም፡፡ 

    አንቀጽ ሃያ ስምንት 

    የጋብቻ ፈቃድ 

    28.1. የፋብሪካው ሠራተኛ ህጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም አምስት /5/ የሥራ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት ለአንድ ጊዜ ብቻ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ 

    28.2. ሠራተኛው የጋብቻ ፈቃድ ሲፈለግ ከ7 /ሰባት/ ቀን በፊት ለሚሰራበት መምሪያ /አገልግሎት/ በፅሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ 

    29.3. ሠራተኛው የጋብቻ ፍቃዱን ጨርሶ ሲመለስ ከሚኖርባቸው ቀበሌ ወይም ህጋዊ ስልጣን ከተሰጣቸው አካሎች ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡  

    አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ

    የዓመት ፈቃድ

    በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡   

    አንቀጽ ሰላሳ

    የሐዘን ፈቃድ

    30.1. ማንኛውም ሠራተኛ የትዳር ጓደኛ ወላጅና እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ የሚቆጠር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ ቢሞትበት ከክፍያ ጋር ሶስት የሥራ ቀናት የሀዘን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ይህም በዓመት ከሰባት ቀናት አይበልጥም፡፡ 

    30.2. ሠራተኛ ሃዘን ሲደርስበት በራሱ ወይም በመልእክት ለቅርብ አለቃው እና ክፍሉ ማሳወቅ አለበት፡፡ 

    ሆኖም የሃዘን ፈቃድ ተቀባይነት የሚያገኘው፡- 

    ሀ/ ባስመዘገበው የቤተሰብ ዝርዝር መሰረት ይሆናል፡፡ በባል ወይም በሚስት/ከሁለት በአንዱ/ የግል ማህደር ላይ ከተመዘገበ የሐዘን ፈቃድ ይሰጣል፡፡  



    አንቀጽ ሰላሳ አንድ

    የወሊድ ፈቃድ

    በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 

    ምዕራፍ 3

    አንቀጽ ሰላሳ ስድስት

    የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች አወሳሰድ፡-

    1. የቅጣት እርምጃዎችና የአቀጣጥ ሥነ ሥርዓት 

    ሀ/ አንድ ሠራተኛ ጥፋት መፈጸሙን የሥራ ኃላፊም ሆነ ሠራተኛ ሲያመለክት ወይም ሪፖርት ሲያደርግ ፋብሪካው ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ከአባሪ አንድ እስከ ሦስት ባሉት መካከል ተፈጻሚነት ያለውን የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወሰዳል፡፡  

    ለ/ ሠራተኛው በዚህ አንቀጽ ያልተጠቀሰ ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ ፋብሪካው ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ይወስድበታል፡፡ 

    ሐ/ ሠራተኛው በሥነ ሥርዓቱ እርምጃ አወሳሰድ ሠንጠረዥ ውስጥ ከሰፈሩት ጥፋቶች መካከል አንዱን ፈጽሞ ለዚህ ጥፋት የሚገባውን ቅጣት ከተሰጠው በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ጥፋት አጥፍቶ ቢገኝ የሚቀጥለው ከፍተኛ የቅጣት እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ 

    መ/ በሥራ ላይ ጥፋት ለፈጸመ ሠራተኛ የቃል ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሠራተኛው የጽሑፍ መተማመኛ እንዲፈርም ይደረጋል፡፡ 

    ሠ/ ሠራተኛ ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ የሥነ ሥርዓት እርምጃ እንዲወሰድበት ለአስተዳደር መምሪያ ጥያቄ የሚያቀርበው ሠራተኛው በሚገኝበት የመምሪያ ኃላፊ ወይም እርሱ በሚወክለው ኃላፊ ይሆናል፡፡ 

    ረ/ ሠራተኛው የቅጣት ሥነ ሥርዓት እርምጃ አንድ ጊዜም ሆነ በመደጋገም ተወስዶበት ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ጥፋት ለአንድ ዓመት ጥፋት ከመፈጸም ተቆጥቦ የቆየ እንደሆነነ የቀድሞ ጥፋቱ ታሳቢ ሆኖ የሥነ ሥርዓት እርምጃው አይወሰድበትም፡፡ ነገር ግን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ ጥፋቶች ለደረጃ ዕድገትና ለአስተዳደራዊ ሥራዎች ታሳቢ ይሆናሉ፡፡

    ሰ/ በዚህ አንቀጽ ተራ ቁጥር 2 ላይ ከተጠቀሱት ጥፋቶች መካከል ሠራተኛው አንደኛውን መፈጸሙ በሚገባ ሲረጋገጥ በቀጥታ ከሥራ ይሰናበታል፡፡ ሆኖም የፋብሪካው አስተዳደር እንደሁኔታው መክበድና መቅለል ቅጣቱን ሊያሻሽለው ይችላል፡፡ 


    1. የቅጣት እርምጃ ሥርዓት 
    1. ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ማሰናበት 

    ሀ/ የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡ 

    1. ያለበቂ ምክንያት ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በመድጋገም የሥራ ሰዓት ያለማክበር፣ 
    2. በመደዳው ለአምስት የሥራ ቀናት ወይም ባንድ ወር በጠቅላላው ለአሥር ቀናት፣ በአንድ ዓመት ውስጥ በጠቅላላው ለሠላሳ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከሥራ መቅረት፣ 
    3. በሥራው ላይ ሠነድ መረጃ መደለዝ፣ መሠረዝ፣ መቀየር፣ ማጥፋት፣ መደበቅ እና ሌሎችም የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር መፈጸም፣ 
    4. ማንኛውም የፋብሪካውን ንብረት ወይም ገንዘብ አላግባብ መጠቀም፣ 
    5. በሥራ ቦታው አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪ ሆኖ መገኘት፣ 
    6. በፋብሪካው ውስጥ በማንኛውም ጊዜ የግል ጥቅም የሚያስገኝ የግል ሥራውን ሲሰራ የተገኘ ወይም የፋብሪካውን ያልሆነውን ማንኛውንም ዕቃ የጠገነ፣ ያጸዳ ወይም የሠራ፣ 
    7. በማንኛውም ዓይነት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንያት ቢያዘው ሥራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት፣ 
    8. በፋብሪካው ንብረት ወይም ከፋብሪካው ጋር ግንኙነት ባለው ማንኛውም የሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ 
    9. በሥራ ላይ ሕይወትንና ንብረትን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት መፈጸም፣ 
    10. ያለፋብሪካው ፈቃድ ከሥራ ቦታ ንብረት መውሰድ፣ 
    11. በሥራ ጊዜ በስካር ወይም አዕምሮን በሚያደነዝዙ ዕጾችና እንክብሎች ተመርዞ በሥራ ቦታ የተገኘ፣ 
    12. የጤና ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን፣ 
    13. ከሰላሳ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእስራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር፣ 
    14. ማንኛውም የድርጅቱን ንብረት ደብቆ ሰርቆ ለማውጣት የሞከረ፣    
    15. በፋብሪካው ምሥጢር ሆነው የተያዙትን ሥራዎች በሰነድ በመዛግብት ወይም በሌላ ሁኔታ ለሌላ ሦስተኛ ወገን ማውጣት፣ መስጠት ወይም ማስተላለፍ፣ 
    16.  ከመሠረታዊ ሠራተኛ ማኀበሩ መደበኛ የስብሰባ ጊዜ በስተቀር ያለ ድርጅቱ እውቅና ስብሰባ ማድረግ ወይም ተመሳሳይ ሕገወጥ ድርጊት መፈፀም፣ 
    17. በማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ማስታወቂያ የገነጠለ፣ 
    18. በድርጅቱና በሠራተኛ ማኅበር ወይም በድርጅቱና በሠራተኞቹ መካከል የኢንዱስትሪ ሰላምን የሚያደፈርስ፣ አለመግባባትና የሚፈጥር ሀሰተኛ ወሬ ማሠራጨት፣ 
    19. ከፋብሪካው ቋሚ ሥራ ወይም የዘለቄታ ጥቅም ጋር ተወዳዳሪ የሆነ ወይም የሚጋጭ ሥራ የሠራ፣ 
    20.  ከድርቱ የተሰጠውን የመታወቂያ ካርድ ሆነ ብሎ ለሌላ ሰው መጠቀሚያ እንዲሆን አሳልፎ የሰጠ፣ 
    1. በማስጠንቀቂያ ከሥራ ማሰናበት 

    የሥራ ውል በማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚቻለው በሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ ነው፡፡  

    ሀ/ ሠራተኛው የተመደበበትን ሥራ ለማከናወን ችሎው ቀንሶ ሲገኝ የሥራ ችሎታውን ለማሻሻል ወይም ፋብሪካው ያዘጋጀውን የትምህርት ዕድል ባለመቀበል ምክንያት ሲሠራ የቆየውን ሥራ ለመቀጠል የሥራ ችሎታ የሌለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ትምህርት ከተሰጠው በኋላ አስፈላጊውን አዲስ የሥራ ችሎታ ለመቅሰም የማይችል ሲሆን፣ 

    ለ/ ሠራተኛው በጤንነት መታወክ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት በስራ ውል የተጣለበትን ግዴታ ለመፈጸም ለዘለቄታው የማይቻል ሆኖ ሲገኝ፣ 

    ሐ/ ሠራተኛ ተዛውሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፣ 

    መ/ ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ ሲሠረዝና ሠራተኛውን ወደ ሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ፣ ወይም በመዋቅር ለውጥ ምክንያት የሠራተኛ መቀነስ የሚያስከትል ሁኔታ ሲፈጠር፣ 

    ሠ/ ሠራተኛው የተሰማራበት ሥራ በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሠራተኛ ቅነሳ የሚያስከትል ሁኔታ ሲፈጠር፣ 

    ረ/ የፋብሪካው የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ትርፍ ሰቀንስ የሚደረግ የሠራተኛ ቅነሳ፣ 

    ሰ/ የፋብሪካውን ምርታማነት ለማሳደግ፣ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሠራተኛ ቅነሳ፣ 







    በተለያዩ የዲሲፕሊን ጉዳዮች የሚወሰዱ የሥነ ሥርዓት እርምጃዎች 

    ተራ.ቁ

    የጥፋት ዓይነት

    ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት

    በሁለተኛ ጊዜ ጥፋት

    ለሦስተኛ ጊዜ ጥፋት

    ለአራተኛ ጊዜ ጥፋት

    ለአምስተኛ ጊዜ ጥፋት

    ለስድስት ጊዜ ጥፋት


    ያለፍቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከ5-15 ደቂቃ የዘገየ 

    የቃለ ማስጠንቀቂያ 

    የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

    የግማሽ ቀን ደመወዝ 

    የ1 ቀን ደመወዝ 

    የሦስት ቀን ደመወዝ 



    ያለፈቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከ15-45 ደቂቃ መዘግየት 

    የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ1 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ2 የቀን ደመወዝ ቅጣትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት  



    ያለፈቃድ ግማሽ ቀን የቀረ 

    የግማሽ ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ2 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ  

    የ5ቀን ደመወዝ ቅጣትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ  

    የ8ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 



    ያለፍቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት ከ1-4 ቀን ከሥራ የቀረ  

    የ1 ቀን ደመወዝና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ3ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ6ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ10 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 



    ያለፍቃድ ወይም ያለበቂ ምክንያት በመደበኛ የሥራ ሰዓት ምድብ ሥራን ትቶ ከግቢ ወጥቶ የሄደና ሲዘዋወር የተገኘ 

    የ1 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ3 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ7 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከስራ ስንብት 



    የግቢውን ዌም የፋብሪካውን ፅዳት የሚያበላሽ ተግባር የፈጸመ 

    የቃል ማስጠንቀቂያ 

    የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የግማሽ ቀን ደመወዝ 

    የ1 ቀን ደመወዝ 

    የ2 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 



    የተመደበበትን ሥራ የሥራ መመሪያ ባለመከተል የሠራ 

    የ1 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ2 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ3 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ4 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 



    በተለይ ተመድቦ የሚሰራበትን መኪናና መሳሪያዎች እንዲሁም የሥራ ቦታ ለማፅዳት ያልተባበረ 

    የ1 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ3 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ7 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 




    የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠራ ታዞ ያለበቂ ምክንያት ከሥራ የቀረና አልሠራም ብሎ የሄደ 

    የ3 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ5 ቀን ደመወዝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 





    የተቀጠረበትን መደበኛ ሥራ እንዲሰራ ሲታዘዝ አልሠራም ያለ 

    እስከ 5 ቀን ከሥራ ማገድ 

    ከሥራ ማሰናበት 






    የድርጅቱ ተሸከርካሪ ወይም ንብረት ያለፍቃድ ለግል ጥቅም ያዋለ

    የ3 ቀን ደመወዝ ቅጣት ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ7 ቀን ደመወዝ ቅጣት ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ለ15 ቀን ከሥራ ማገድ ከመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ከሥራ ማሰናበት 




    በሾፌርነት የተቀጠረ ሠራተኛ አደጋ ከደረሰ በኢንሹራንስ ውሉ ላይ የማይሸፍነውን ወጭ ሾፌሩ ይሸፍናል 

    የቃለ ማስጠንቀቂያ 

    የ2 ቀን ደመወዝ ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ4 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ6 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ከሥራ ማሰናበት 



    ከድርጅቱን መኪና በራሱ ጥፋት የገጨ ወይም ያስገጨ ሾፌር፣ መካኒክ ወይም ሌላ ሠራተኛ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመው በቀር በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት ካላደረገና ለመድን ድርጅት ሪፖርት ማድረጊያውን ጊዜ ካሳለፈ 

    የመኪናውን ማሰሪያ ወጪና የ3 ቀን ደመወዝ ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የመኪናውን ማሰሪያ ወጪ ከፍሎ ከሥራ ማሰናበት 






    በሥራ ላይ ተኝቶ የተገኘ 

    የ3 ቀን ደመወዝና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 





    በፈረቃ ሥራ ላይ የደንብ ልብስ ለብሶ ያልተገኘ 

    የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ1 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ2 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ4 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 




    በፈረቃ ሥራ በማሽኖች ላይ ለሚሰሩና በጥበቃ ሥራ ላይ የተመደቡ ሠራተኞች የኝተው ከተገኙ 

    የ5 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ10 ቀን ደመወዝና  የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 





    በቸልተኝነት ሠራተኛው እውነተኛውን የሥ ውጤት ያለበቂ ምክንያት ሳይመዘግብ ወይም ሳያመለክት ከቀረ 

    የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ  

    የ10 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 




    በሥራው ላይ ግዴለሽነት፣ ትጋት ጥንቃቄ የጎደለው ሥራ የሰራ ላደረሰው ጉዳት ተጠያቂ ሆኖ  

    የ2 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ4 ቀን ደመወዝ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ6 ቀን ደመወዝ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 




    ያለፍቃድ ወይም ያለምድብ ሥራ መኪናዎችን በመነካካት ጉዳት ወይም ብልሽት ያደረሰ ላደረሰው ጉዳት በገንዘብ ተተምኖ ከፋይ ሆኖ 

    የ7 ቀን ደመወዝ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ከሥራ ስንብት 






    የሌላውን ሠራኛ የሰዓት መቆጣጠሪያ የመታ ወይም አስመስሎ የፈረመ ወይም የራሱን ያስመታ ወይም ያስፈረመ 

    የ2 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ5 ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ከሥራ ማሰናበት 





    ከበላይ የተሰጠውን ወይም ከቅርብ አለቃው የተሰጠውን ተገቢ ትእዛዝ ወይም መመሪያ ሳይፈጽም የቀረ  

    የ2 ቀን ደመወዝ ከጽሑፍ ማጠንቀቂያ ጋር 

    የ5ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    ከሥራ ማሰናበት 





    አልፈተሸም ብሎ የገባ ወይም የወጣ 

    የ2 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር

    ከሥራ ማሰናበት 





    የፋብሪካውን ሠራተኞች የሰደበ 

    የ2ቀን ደመወዝ ከሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋር 

    የ4 ቀን ደመወዝ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጋ 

    የ8 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 




    የሥራ ኃላፊዎን የተሳደበና ያመናጨቀ 

    የ3 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 





    ባልተፈቀደ ወይም በተከለከለ ቦታ በጋራ ያጨሰ 

    የ8 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 






    በፋብሪካው ውስጥ በገንዘብ ቁማር የተጫወተ 

    የ3 ቀን ደመወዝና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    የ5 ቀን ደመወዝና የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 

    ከሥራ ማሰናበት 





    ባለው የሥራ ፀባይ ምክንያት በፋብሪካው ሠራተኞች መካከል አንዱን ካንዱ በማበላለጥ አድልኦ ያለበት የአሠራር አፈጻጸም ማድረጉ የተረጋገጠበት










     



     





     

        

    ከሥራ ስለማገድ 

    ሀ/ በፋብሪካው ላይ አደጋ ሲሚደርስበት ወይም በደረሰበት ጥፋት የተነሳ ወይም በእምነት ማጉደል ድርጊት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ እንዲሁም ከፋብሪካው ጋር በተገናኘ ሁኔታ በወንጀል ጥፋት በሕግ ተከሶ የተመሰከረበት ሠራተኛ ሁኔታው ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ሊታገድ ይችላል፡፡ ሆኖም ጥፋቱ ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጣርቶ እንዲቀርብ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡ ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ ያጠፋው ጥፋት ተዘርዝሮ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ 

    ለ/ የአገዳውን ጊዜ ማራዘም ሲያስፈልግ አስቀድሞ ለጥያቄው ተገቢውን ምክንያት ለፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ በማቅረብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲፈቅድ የእገዳውን ጊዜ ማራዘም ይቻላል፡፡ ሆኖም ስለእገዳው መራዘም ወይም አለመራዘም ውሳኔው ከአስራ አምስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መስጠት ይኖርበታል፡፡ 

    ሐ/ የዕገዳ ጊዜ በማንኛውም ጊዜ ከሦስት ወር በላይ ሊበልጥ አይችልም፡፡ 

    መ/ አንድ ሠራተኛ ከታገደ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት የሚያበቁት ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው በወቅቱ ማራዘሚያ ፈቃድ መጠየቅ የሚገባው አካል ተገቢውን ባለመፈጸሙ በኃላፊነት ይጠየቃል፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ ሠራተኛውን ከጥፋቱ ነፃ ሊያደርገው አይችልም፡፡ 

    ሠ/ ሠራተኛው ከሥራ ታግዶ እንዲቆይ ሲያስፈልግ ምክንያት ተዘርዝሮ ይጻፍለታል፡፡ 

    ረ/ የማገጃውን ትዕዛዝ ለሠራተኛው ለመስጠት የማይቻልበት ምክንያት ካለ በፋብሪካው የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ለአስር ቀን ተለጥፎ ይቆያል፡፡ እገዳውም የሚጸናው የማገጃው ደብዳቤ በደረሰኝ ለሠራተኛው ከተሰጠበት ወይም በማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ዕለት ማግስት ጀምሮ ይሆናል፡፡ 

    ሰ/ የታገደ ሠራተኛ በዕገዳው ወቅት ሥራውንና ለሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን፣ ሠነዶችን ለዕገዳው ምክንያት መነሻ ወይም ለሠራተኛው የመከላከያ ማስረጃነት የሚያስፈልገው ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ 

    ሸ/ አንድ ሠራተኛ ከሥራ ሲታገድ ከሥራው ታግዶ ለሚቆይበት ጊዜ ደመወዙ መያዝ አለበት፡፡ ሆኖም እንደጉዳይ ሁኔታ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለታገደው ሰራተኛ ከወር ደመወዙ እስከ ግማሽ እንደ ሁኔታው ሊፈቅድ ይችላል፡፡ 

    ቀ/ የታገደ ሠራተኛ በውሳኔ ነፃ ሆኖ ሲገኝ በቀጥታ ወደ ስራው እንዲመለስ ይደረጋል፡፡ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ ግን እንደጥፋቱ ደረጃ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ 

    በ/ በተከሰሰበት ወንጀል ወይም በዲሲፕሊን ክስ በሚሰጠው ውሳኔ ሠራተኛው ጥፋተኛ ሆኖ ካልተገኘ ታግዶ ለቆየበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ በሙሉ ያለወለድ ይከፈለዋል፡፡   

    Zong Eth Textile Factory - 2018

    Start date: → 2018-01-01
    End date: → Not specified
    Name industry: → Manufacturing
    Name industry: → Manufacture of textiles, Manufacture of wearing apparel
    Public/private sector: → In the private sector
    Concluded by:
    Name company: →  Zong Eth Textile Factory
    Names trade unions: →  ዞንግ ኢት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኛ ማህበር

    TRAINING

    Training programmes: → Yes
    Apprenticeships: → No
    Employer contributes to training fund for employees: → Yes

    WORK AND FAMILY ARRANGEMENTS

    Maternity paid leave: → -9 weeks
    Job security after maternity leave: → No
    Prohibition of discrimination related to maternity: → No
    Prohibition to oblige pregnant or breastfeeding workers to perform dangerous or unhealthy work: → 
    Workplace risk assessment on the safety and health of pregnant or nursing women: → 
    Availability of alternatives to dangerous or unhealthy work for pregnant or breastfeeding workers: → 
    Time off for prenatal medical examinations: → 
    Prohibition of screening for pregnancy before regularising non-standard workers: → 
    Prohibition of screening for pregnancy before promotion: → 
    Facilities for nursing mothers: → No
    Employer-provided childcare facilities: → No
    Employer-subsidized childcare facilities: → No
    Monetary tuition/subsidy for children's education: → No
    Leave duration in days in case of death of a relative: → 7 days

    GENDER EQUALITY ISSUES

    Equal pay for work of equal value: → No
    Discrimination at work clauses: → Yes
    Equal opportunities for promotion for women: → No
    Equal opportunities for training and retraining for women: → No
    Gender equality trade union officer at the workplace: → No
    Clauses on sexual harassment at work: → No
    Clauses on violence at work: → Yes
    Special leave for workers subjected to domestic or intimate partner violence: → No
    Support for women workers with disabilities: → No
    Gender equality monitoring: → No

    EMPLOYMENT CONTRACTS

    Trial period duration: → 40 days
    Part-time workers excluded from any provision: → No
    Provisions about temporary workers: → No
    Apprentices excluded from any provision: → No
    Minijobs/student jobs excluded from any provision: → No

    WORKING HOURS, SCHEDULES AND HOLIDAYS

    Working hours per day: → 8.0
    Working hours per week: → 48.0
    Working days per week: → 6.0
    Paid annual leave: →  days
    Paid annual leave: →  weeks
    Fixed days for paid annual leave: → 13.0 days
    Rest period of at least one day per week agreed: → Yes
    Provisions on flexible work arrangements: → No

    WAGES

    Wages determined by means of pay scales: → No
    Adjustment for rising costs of living: → 

    Wage increase

    Once only extra payment

    Once only extra payment due to company performance: → No

    Meal vouchers

    Meal allowances provided: → No
    Free legal assistance: → No
    Loading...